በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኡጋንዳ በአዲስ ዓመት በዓል አከባበር ላይ 9 ሰዎች ሞቱ


በኡጋንዳ የአዲስ ዓመት አቀባበል (ፎቶ ኤ.ኤፍ.ፒ)
በኡጋንዳ የአዲስ ዓመት አቀባበል (ፎቶ ኤ.ኤፍ.ፒ)

በኡጋንዳ በአዲስ ዓመት አከባበር ላይ በተፈጠረ መጨናነቅ 9 ሰዎች መሞታቸውን ፖሊስ አስታውቋል።

ከሟቾቹ አብዛኞቹ ከ10 እስከ 20 ዓመት እድሜ ያላቸው ናቸው ተብሏል።

በመዲናዋ ካምፓላ በአንድ የገበያ ሥፍራ (ሞል) አቅራቢያ የነበረን የርችት ተኩስ ለመመልከት የተሰባሰቡት ሰዎች ሲጋፉ በተፈጠረ መረጋገጥ 5 ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ አራቱ ደግሞ ወደ ሆስፒታል በመወሰድ ላይ ሳሉ ህይወታቸው አልፏል ሲል ኤ.ኤፍ.ፒ ዘግቧል። በርካታ ሰዎችም ተጎድተዋል።

ከሶስት ዓመት መቋረጥ በኋላ አዲሱን ዓመት በፌስታ ለመቀበል የተሰባሰቡት እድምተኞች ከፍ ካለ ቦታ ርችቱን ከተመለከቱ በኋላ ወደታች ሲወርዱ በተፈጠረ ግፍያ አደጋው ሊፈጠር ችሏል።

XS
SM
MD
LG