በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዓለም 2023ትን በደማቁ ተቀበለች


በኒው ዮርክ ታይም ስኩዬር የአዲስ ዓመት አከባበር (ፎቶ ሮይተርስ)
በኒው ዮርክ ታይም ስኩዬር የአዲስ ዓመት አከባበር (ፎቶ ሮይተርስ)

ዓለም አዲሱን የአውሮፓውያን ዓመት በደማቅ አከባበር ተቀብላለች።

ከኒው ዮርኮ ታይምስ ስኩዬር እስከ አውሮፓና እሲያ ታላላቅ ከተሞች አዲሱን 2023 በርችትና በፈንጥዝያ ተቀብለዋል።

አውሮፓውያኑ በዩክሬን ያለው ጦርነት በአዲሱ ዓመት እንዲያበቃ ሲመኙ፣ እሲያውያኑ ደግሞ ከኮሮና ወረርሽኝ ሙሉ ለሙሉ የሚላቀቁበት ዓመት እንዲሆን ተመኝተዋል።

በአሜሪካ፣ ኒው ዮርክ ከተማ ከሁለት ዓመት በኋላ ካለምንም ገደብ በዓሉ ተከብሯል። በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ባለፉት ሁለት ዓመታት አዲስ ዓመት የተከበረው እንደነገሩ ነበር።

በታይምስ ስኩዬር ዝናቡ ሲወርድ ቢውልም ለሰዓታት ተፋፍገው ሲጥብቁ የነበሩት እድምተኞች ብልጭልጯ ኳስ 25 ፎቅ ካለው ህንጻ ቁልቁል ወርዳ ታች ስትቆም አዲሱን ዓመት እንኳን ደህና መጣህ ብለዋል።

በእንግሊዝ፣ ለንደን ከተማ “የለንደን ዓይን” ብለው የሚጠሩት ማማ ሰማያዊና ቢጫ ቀለማትን ፈንጥቋል። ከዩክሬን ጋር ያላቸውን አንድነትና ድጋፍ ለማሳየት ነው ተብሏል።

አሮጌው 2022 በጦርነት፣ በኢኮኖሚ ቀውስ እና በዓለም ሙቀት መጨመር ሲታወስ፣ በመልካም ጎኑ ደግሞ ድራማ የተሞላበትና ከመቀመጫ ቁጭ ብድግ ያደረገንን የዓለም ዋንጫ ያየንበትና በቴክኖሎጂ መስክ ፈጣን ዕድገቶች የተመዘገቡበት ሆኖ አልፏል።

XS
SM
MD
LG