በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራንና ሩሲያ የኒውክሌር ንግግሮች እድል ለዘለአለም እንደማይኖር አስጠነቀቁ


በዮርዳኖስ ንጉሣዊ ቤተ መንግሥት የተለቀቀው ፎቶ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሁሴን አሚር አብዶላሂ በጆርዳን በተካሄደው የባግዳድ ትብብር እና አጋርነት ስብሰባ ላይ ንግግር ሲያደርጉ ያሳያል። ታህሳስ 20፣ 2022
በዮርዳኖስ ንጉሣዊ ቤተ መንግሥት የተለቀቀው ፎቶ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሁሴን አሚር አብዶላሂ በጆርዳን በተካሄደው የባግዳድ ትብብር እና አጋርነት ስብሰባ ላይ ንግግር ሲያደርጉ ያሳያል። ታህሳስ 20፣ 2022

ሩሲያ እና ኢራን፣ በኒውክለር ዙሪያ ከኢራን ጋር የሚደረገውን ድርድር በድጋሚ አለመጀመር ሊኖረው ስለሚችለው አደጋ በቅርቡ አስጠንቅቀዋል። ሆኖም በቅርቡ በኢራን የተካሄደውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተቃውሞ እና ሩሲያ በዩክሬን ላይ ያካሄደችውን ጦርነት ተከትሎ የምዕራባውያን ሀገሮች ድርድሩን ለመቀጠል ፍላጎት እንደሌላቸው ሁለቱም ሀገሮች በተናጠል ገልፀዋል።

መቀመጫውን ቪየና ያደረገው ዓለም አቀፉ የአውቶሚክ ኤነርጂ ተቋም ኢራን በሳተላይት ምስል የተደረሰበትና ይፋ ያላደረገችው ሰው ሰራሽ ዩራኒየም በሶስት ስፍራዎች ስለመገኘታቸው ጉዳይ እንድታብራራ ለረጅም ጊዜ ሲጠይቅ ቢቆይም ኢራን ያንን አላደረገችም፡፡

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ትላንት ሀሙስ ለመንግሥት መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ሞስኮ ዩናይትድ ስቴትስና አጋሮችዋ ከኢራን ጋር ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ትደግፋለች ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ከኢራን ጋር ከኒውክለር ስምምነት አለመድረስ ውጥረቱን ሊያባብስ፣ የጦር መሳሪያ እሽቅቅድምና ግልጽ ግጭት ሊፈጥር እንዲሁም የማይቀለበሱ መዘዞችን ሊያስከትል እንደሚችል ላቭሮቭ አስጠንቅቀዋል፡፡

ሩሲያ የጋራ ሁለንተናዊ የድርጊት መርሃ ግብሩን እንደገና ለማደስ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሚና ቢኖራትም፣ ከሩሲያው የዩክሬን ወረራ ወዲህ ሞስኮ ከቴህራን ጋር ያላትን ግንኙነት ማጥበቋ ተገልጿል፡፡

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሁሴን አሚር አቡዱላሂን በቅርቡ ከኦማን ጉብኝታቸው መልስ በሰጡት መግለጫ ከኢራን ጋር ከስምምነት ለመድረስ የተከፈተው የእድል መስኮት ሁሌም ክፍት ሆኖ አይቆይም ብለዋል፡፡

ኦማን ኢራን እና ዩናይትድ ስቴትስ ከስምምነት እንዲደርሱ ስታሸማግል መቆየቷ የተገነረ ቢሆንም አዲሱ የኦማን ሱልጣን የተደራዳሪዎቹን መልዕክት ለኢራን በትክክል ስለማድረሳቸው እርግጠኛ መሆን እንዳልተቻለ ሮይተርስ አመልክቷል፡፡

የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ክርስቶፈር በርገር “በእኛ አስተያየት በአሁኑ ጊዜ ከኢራን ጋር የሚደረገው የኒውክለር ድርድር እንደሚቀጥል የሚያሳይ ምልክትም ሆነ ምክንያት የለም” ሲሉ መናገራቸው ተመልክቷል፡፡ አክለውም ይልቁንም ጀርመን ትኩረት ያደረገቸው በክብርና በነጻነት መኖርን በመሻት በኢራን አደባባዮች ለተቃውሞ በወጡ ሰዎች ላይ ነው ማለታቸው ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG