በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዳርፉር ግጭት ስምንት ተገደሉ


ዳርፉር ሱዳን
ዳርፉር ሱዳን

በሱዳን ምዕራባዊ ዳርፉር ክልል ውስጥ ሪዚጋት በተሰኘው የአረብ ጎሳ እና ፉር ጉሳ መካከል በተፈጠረ ግጭት ስምንት ሰዎች መገደላቸውን አንድ የዕርዳታ ድርጅት አስታወቀ።

በማዕከላዊ ዳርፉር መዲና አንድ የፉር ጎሳ አባል ከተገደለ በኋላ በሁለቱ ወገኖች መከከል ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል።

የፉር ጎሳ አባሉ ከተገደለ በኋላ ሪዚጋት የአረብ ጎሳ ዓባላት በሞተር ብስክሌት ላይ በመሆን በአንድ የተፈናቃዮች መጠለያ በመግባት የፉር ጎሳ ዓባላትን አጥቅተዋል ሲሉ በሱዳን የአንድ ፍልሰተኞችና ተፈናቃዮች አስተባባሪ ቡድን ቃል አቀባይ አዳም ሬጋል ለ ኤ.ኤፍ.ፒ ተናግረዋል።

በግጭቱ ስምንት ሰዎች ሲገደሉ 11 መቁሰላቸውን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል ።

ከ 20 ዓመታት በፊት በሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት ከተጫረ በኋላ የአውቶማቲክ መሣሪያዎች እንደልብ መገኘት በጎሳዎች መካከል በቀላሉ ግጭት እንዲቀሰቀስ አንዱ ምክንያት ሆኗል ተብሏል።

የእርስ በእርስ ጦርነቱ እዳጣን ጎሳዎች በአረቦች የበላይነት ተይዞ ከበነበረው የኦማር አል-በሽር መንግስት ጋር ግጭት ውስጥ እንዲገቡም አድርጓል።

የተመድ እንደሚለው በሱዳኑ ግጭት ወደ 300 ሺህ ሰዎች ሲገደሉ 2.5 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ተፈናቅለዋል።

XS
SM
MD
LG