በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፔፕፋር ኤችአይቪ/ኤድስን በመከላከልና በመቆጣጥር ከፍተኛ ውጤት ማስገኘቱን ገለፀ


ፔፕፋር ኤችአይቪ/ኤድስን በመከላከልና በመቆጣጥር ከፍተኛ ውጤት ማስገኘቱን ገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:20 0:00

ፔፕፋር ኤችአይቪ/ኤድስን በመከላከልና በመቆጣጥር ከፍተኛ ውጤት ማስገኘቱን ገለፀ

ኤችአይቪ/ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በኢትዮጵያ ላለፉት 19 ዓመታት በኢትዮጵያ የተከናወነው ሥራ ከፍተኛ ውጤት ማስገኘቱን በኢትዮጵያ የፔፕፋር ሥራ አስተባባሪ አስታወቁ።

ኤድስን ለመከላከል የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት አስቸኳይ እቅድ ወይም ፔፕፋር መርኃ ግብር ኤችአይቪ/ኤድስን በመመከትና በመቆጣጠር በኩል ከፍተኛ ስኬት ማስመዝገቡን በኢትዮጵያ የፔፕፋር አስተባባሪዋ ዶ/ር ኤሚ ሩራንግዋ ገልፀዋል።

ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ለዚህ መርኃ ግብር ወደ 3 ቢሊዮን ዶላር ወጥቶበታል። ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ሕፃናትን ጨምሮ ከ456 ሺህ 348 በላይ ወንዶችና ሴቶች የፀረ ኤድስ መድኃኒት በመስጠት ሕይወታቸውን ታድጓል።

ካለፈው መስከረም ጀምሮ ከ2.4 ሚሊዮን በላይ ሰው የምርመራና የማማከር አገልግሎት እንዲያገኙ አድርጓል። እየተገባደደ በሚገኘው የአውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር ወላጆቻቸውን ላጡና ለጉዳት ተጋላጭ ለሆኑ ሕፃናት ድጋፍ መስጠቱም ተገልጿል።

በአጠቃላይ ኤችአይቪ/ኤድስን በመቆጣጠር በኩል የተገኘውን መልካም ውጤት ዘላቂነት ለማረጋገጥ በትኩረትና በብርቱ መሥራት እንደሚያስፈልግ አስተባባሪዋ ዶ/ር ኤሚ ሩራንግዋ አሳስበዋል።

/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG