በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያ ሚሳይሎች ኬርሰንን ዒላም አድርገዋል - ዩክሬን


በዩክሬን በባክሙት ከተማ ዳርቻ ከደረሰ የሩሲያ ጥቃት በኋላ ይታይ የነበረው ጭስ - ታህሳስ 27, 2022.
በዩክሬን በባክሙት ከተማ ዳርቻ ከደረሰ የሩሲያ ጥቃት በኋላ ይታይ የነበረው ጭስ - ታህሳስ 27, 2022.

ሩሲያ ረቡዕ እለት የተኮሰቻቸው ሚሳይሎች በኬርሰን ደቡባዊ የከተማው ክፍል የሚኖሩ ሲቪሎችን ዒላማ ያደረጉ ነበሩ ስትል ዩክሬን ከሳለች።

የሩሲያ ኃይሎች ባለፈው ወር ጥለው ከወጡ በኃላ ዩክሬን ዳግም በተቆጣጠረችው ኬርሰን ግዛት ላይ 33 ሚሳይል መተኮሳቸውን የዩክሬን ጦር ኃይሎች አጠቃላይ ሰራተኞች ያስታወቁ ሲሆን ሩሲያ ግን ሲቪሎችን ዒላማ አላደረኩም ስትል ክሱን አስተባብላለች።


ከዚህ ጋር በተያያዘ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሀገራቸው በዚህ ወር መጀመሪያ ተግባራዊ የተደረገውን እና በምዕራባውያን ሀገራት ለተጣለው የነዳጅ ዋጋ ጣሪያ ስምምነታቸውን ለሰጡ ሀገራት ማንኛውንም አይነት ነዳጅ መላክ እንደምትከለክል ማክሰኞ እለት አስታውቀዋል።

አዋጁ "ዩናይትድ ስቴትስ፣ ሌሎች የውጭ ሀገራት እና እነሱን የተቀላቀሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ለወሰዱት ጠብ አጫሪ እና ዓለም አቀፍ ህግጋትን የጣሰ ርምጃ" ቀጥተኛ ምላሽ ተደርጎ መቅረቡን ሮይተርስ ዘግቧል። የነዳጅ ዋጋ ጣሪያ ተመኑ የተቀመጠው ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ጃፓን፣ እንግሊዝን እና ዩናይትድ ስቴትስን ባካተተ የሰባት ሀገራት እና የአውሮፕ ህብረት ስምምንት መሰረት ሲሆን በቡድን ሰባት ሀገራት፣ በአውሮፓ ህብረት እና በአውስትራሊያ ተፈፃሚ እንደሚሆን ሮይተርስ ጨምሮ ገልጿል።

ሩሲያ በበኩሏ የዋጋ ጣሪያ መቀመጡ በዩክሬን የምታደርገውን ወታደራዊ ዘመቻ እንዳማይጎዳው በመግለፅ፣ ለነዳጅ ምርቶቿ አዳዲስ ገዢዎችን እንደምታገኝ ያላትን እምነት አስታውቃለች።

XS
SM
MD
LG