በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጨጓራ እና የትልቁ አንጀት ጤና


የጨጓራ እና የትልቁ አንጀት ጤና
please wait

No media source currently available

0:00 0:14:49 0:00

ስለ ሆድ ህመም ስናነሳ አብዛኛውን ጊዜ ከአመጋገብ አንስቶ እስከ መጻዳጃ ቤት መጠቀም ድረስ ካለው ሁኔታ ጋር ይያያዛል፡፡ አብዛናውን ጊዜ የሆድ ህመም በቀላሉ የሚደን የጋዝ መጠራቀም ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ አንዳንዴ ደግሞ የሆድ ህመም አስጊ የሆነ ከምግብ መፈጨት ጋር የተያያዘ ህመም ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡

በተለያዩ ጊዜያት የተስሩ ጥናቶች በዓለም ዙሪያ ከአስር አዋቂዎች አራቱ በትልቁ አንጀት ህመም እንደሚጠቁ ያመላክታሉ፡፡ የምግብ መፈጨት ስርዓት ትንሹን እና ትልቁን አንጀት፣ ጣፊያ፣ ጉበት፣ ጨጓራን እንዲሁም ደግሞ የሃሞት ከረጢትን ያጠቃልላል፡፡ እነዚህ አካላትም ወደ ሰውነት ውሃን ማዋሃድን፣ መዓድን እና ቪታሚኖችን ማዋሃድን እንዲሁም ደግሞ ከሰውነት አላስፈላጊ ቆሻሻዎችን ማስወገድን የመሳሰሉ ስራዎች አሏቸው፡፡

ሆድ እቃ ላይ አለመመቸት ሲሰማን፣ ያልታሰብ ክብደት መቀነስ፣ የአሲድ መረጨት፣ የሆድ ድርቀት እና የምግብ ፍላጎት ማጣት በእነዚህ አካላት ላይ ጤናማ ያልሆን ነገር እንዳለ የሚያሳዩ ምልክቶች ናቸው፡፡ ይህ ሁኔታ ሲፈጠርም ሃኪሞች ኢንዶስኮፒ በመባል የሚታወቀውን እና በሰውነት ውስጥ በአፍ አሊያም በፊንጢጣ ተገብቶ ህመሙ ምን እንደሆነ የሚታይበትን የምርመራ ዘዴን ይጠቀማሉ፡፡

በዚህ መሰናዷችን የባለሞያ ምክር እና በአጠቃላይ ስለ ጨጓራ እና ስለ ትልቁ አንጀት ማወቅ የሚገቡን ነገሮች ተካተዋል።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው የምስል ፋይል ያግኙ/

XS
SM
MD
LG