በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢራን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሞት የተፈረደባቸውን ሁለት ተቃዋሚዎች ይግባኝ ተቀበለ


በኢራን እየተካሄደ ባለው ተቃውሞ እንደሞቱ የተገለፁ ሰዎችን ለማሰብ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ምክርቤት አቅራቢያ የተደረገ የሻማ ማብራት ስነስርዓት ታህሳስ 17, 2022
በኢራን እየተካሄደ ባለው ተቃውሞ እንደሞቱ የተገለፁ ሰዎችን ለማሰብ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ምክርቤት አቅራቢያ የተደረገ የሻማ ማብራት ስነስርዓት ታህሳስ 17, 2022

የኢራን ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ሁለት ተቃዋሚዎች ከፍተኛው ፍርድቤት ጉዳያቸውን ያጣራበት ሂደት ጉድለት ነበረው በማለት የይግባኝ ጥያቄያቸውን መቀበሉን የሀገሪቱ የፍትህ አካላት ዛሬ አስታወቁ።

የፍትህ አካሉ ዜና ወኪል የሆነው ሚዛን የዜና አገልግሎት "በምርመራ ጉድለቶች ምክንያት፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እንደገና እንዲመረመር ወደ ተመሳሳይ ፍርድቤቶች መርቷቸዋል" ሲል ዘግቧል።

ኢራን በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ሁለት ተቃዋሚዎችን በስቅላት የቀጣች ሲሆን፣ የ23 አመቱ ሞህሰን ሸካሪ በመስከረም ወር በተካሄደ ተቃውሞ ዋናውን መንገድ በመዝጋት እና አንድ የፀጥታ ኃይል አባል በቢላ ወግቶ በማቁሰል ነበር የተከሰሰው። ሌላው የ23 አመት ወጣት ማጂዲ ሬዛም እንዲሁ የፀጥታ አባል ወግቶ በመግደል ተፈርዶበት በስቅላት ተቀጥቷል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል እንዳለው ሰዎች በመላው ኢራን በተቀጣጠለው የተቃውሞ ሰልፎች እንዳይካፈሉ ለማስፈራራት የኢራን ባለስልጣናት ቢያንስ 21 ሰዎች በሞት እንዲቀጡ ጠይቀዋል።

አንድ ከፍተኛ የመንግስት ፀጥታ አካል በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ እንዳስታወቀው በኢራን በተከሰተው አለመረጋጋት የፀጥታ ኃይሎችን ጨምሮ ቢያንስ 200 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

XS
SM
MD
LG