በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኒጀር ወታደሮች በደቡብ ምስራቅ 5 ጂሀዲስት ተዋጊዎችን መግደላቸው ተገለፀ


በኒጀር የዲፋ ክልል እና አካባቢውን የሚያሳይ ካርታ
በኒጀር የዲፋ ክልል እና አካባቢውን የሚያሳይ ካርታ

በደቡብ ምስራቅ ኒጀር በናይጄሪያ ድንበር አቅራቢያ በተፈጠረ ግጭት አምስት የቦኮ ሀራም ጂሃዲስት ተዋጊዎች መገደላቸውን እና ሁለት የኒጀር ወታደሮች መቁሰላቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አርብ እለት አስታወቁ።

ወታደሮቹ ከጂሃዲስት ተዋጊዎቹ ጋር የተጋጩት በዲፋ ክልል ውስጥ በሚገኙት ባግዊ እና ቾንጉዋ በተሰኙ ከተሞች ውስጥ ነው።

ባለፈው ወር ክልሉን እንዲያስተዳድሩ የተሾሙት ሳሚን ዩኑስ እንዳሉት በአሁኑ ሰዓት ወታደራዊ ሀይሉ ሙሉውን አካባቢ እየተቆጣጠረ ነው። ለበርካታ ሳምንታት ግጭት ሳይታይበት የሰነበተው ዲፋ ክልል በዚህ አመት
ከዮቤ ወንዝ በተነሳ ጎርፍ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል።

ከቦኮ ሀራም ስጋት በተጨማሪ ኒጀር በስተምዕራብ በታላቁ ሰሃራ ከሚገኘው እስላማዊ መንግስት ጨምሮ ከሳሄሊያን ጂሃዲስት ቡድኖች ተደጋጋሚ ጥቃት ይደርስባታል።

በዲፋ ክልል 300 ሺህ ናይጄሪያን ስደተኞች እና ሌሎች ቦኮ ሀራምንና እስላማዊው መንግስት በምዕራብ አፍሪካ የሚያደርሰውን ጥቃት ሸሽተው የተሰደዱ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ይኖሩባታል።

XS
SM
MD
LG