በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአል-ሻባብ ተፈፀመ በተባለ ጥቃት አንድ ፖሊስ እና ሌላ ሲቪል ተገደሉ 


ፋይል- የኬንያ ፖሊስ ኃላፊ የሰዓት እላፊውን ተላልፏል ያለን መገደኛ አስቁሞ ሲያነጋግር።
ፋይል- የኬንያ ፖሊስ ኃላፊ የሰዓት እላፊውን ተላልፏል ያለን መገደኛ አስቁሞ ሲያነጋግር።

በምሥራቅ ኬንያ ከሶማሊያ ጋራ በምትዋሰነው ጋሪሳ በተባለች ስፍራ ትናንት ለተገደሉት አንድ የፖሊስ አባልና አንድ ሲቪል ተጠያቂው አል-ሻባብ ነው ሲል የአካባቢው ፖሊስ አስታውቋል።

ስድስት ሰዎችን ይዞ ሲጓዝ የነበረው የፖሊስ መኪና የተቀበረ ፈንጂ ላይ ሲወጣ ሁለቱ ሰዎች ህይወታቸውን ማጣቸውን የአካባቢው ፖሊስ አዛዥ ተናግረዋል። አዛዡ ለቪኦኤ በስልክ እንደነገሩት የተጎዱ ሌሎች ሶስት ሰዎች በሄሊኮፕተር ወደ መዲናዋ ናይሮቢ ለህክምና ተወስደዋል።

ከጥቃቱ ጀርባ አል-ሻባብ እንዳለና አንድ የጸጥታ ቡድንም የቡድኑን ተዋጊዎቹን በማሰስ ላይ ነው ብለዋል አዛዡ። የትናንቱ ጥቃቱ የመጣው በአል-ሻባብ ሳይፈጸም አይቀርም በተባለ ጥቃት በአንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ የሚገኝ የሬዲዮ መገናኛ አንቴና ከጥቂት ቀናት በፊት ከወደመ በኋላ ነው።

ኬንያ ከአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይላ ጋር የሚያገለግን ሰራዊት ወደ ሶማሊያ ከላከች ጀምሮ፣ መሠረቱን በሶማሊያ ያደረገው አል-ሻባብ በኬንያ ላለፉት 10 ዓመታት ሲንቀሳቀስ ቆይቷል።

XS
SM
MD
LG