በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኡጋንዳ ተጨማሪ የኢቦላ ክትባት ተረከበች

ፋይል - የኡጋንዳ ጤና ሚኒስትር ጄን ሩት አሰንግ ለሱዳኑ ዝርያ የኢቦላ ቫይረስ መከላከያ የሚውለውን የመጀመሪያ ዙር ክትባት በዩጋንዳ፣ ኢንቴቤ ሲረከቡ Dec. 8, 2022.
ፋይል - የኡጋንዳ ጤና ሚኒስትር ጄን ሩት አሰንግ ለሱዳኑ ዝርያ የኢቦላ ቫይረስ መከላከያ የሚውለውን የመጀመሪያ ዙር ክትባት በዩጋንዳ፣ ኢንቴቤ ሲረከቡ Dec. 8, 2022.

ኡጋንዳ ሁለት ተጨማሪ የኢቦላ ክትባት ዓይነቶች ዛሬ ተረክባለች። ‘የሱዳን ኢቦላ ‘ ብለው ለሚጠሩት የኢቦላ ዓይነት የሙከራ ክትባት ነው ተብሏል።

በዩጋንዳ የኢቦላ ወረርሽኝ መግባቱ ከታወቀበት ካለፈው መስከረም ወር ወዲህ 55 ሰዎች በተውሳኩ ሲሞቱ፣ 142 ደግሞ መያዛቸው ታውቋል።

የአሜሪካ ድምጿ ሃሊማ አቱማኒ ከሥፍራው እንደዘገበችው፣ የዓለም ጤና ድርጅት ዛሬ ያስረከበው 4000 የሚሆኑ ክትባቶችን ነው።

ባለፈው ሳምንት ከአሜሪካ ተቋም የተላከ 1000 ክትባት ኡጋንዳ ደርሶ ነበር።

ላለፉት አራት ሳምንታት በኡጋንዳ አዲስ በበሽታው የተያዘ ሰው አለመኖሩ ቢገለፅም፣ አገሪቱ ከኢቦላ ነጻ ነኝ ብላ ለማወጅ ለሚቀጥሉት 20 ቀናት መጠበቅ ይኖርባታል ተብሏል።

XS
SM
MD
LG