በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ተከስቶ የነበረዉ የኮሌራ በሽታ ወደ አጎራባች ዞኖች እየተስፋፋ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ ( ኦቻ) ገለፀ።
በባሌ ዞን አምስት ወረዳዎችና በአጎራባች የሶማሌ ክልል የተከሰተው የኮሌራ በሽታ ወደ ጉጂ ዞን፣ ግርጃ ወረዳ መስፋፋቱንም ድርጅቱ ትላንት ባወጣዉ መግለጫ አመልክቷል ።
ከሰባት መቶ አርባ ሺህ በላይ ሰዎች ለበሽታዉ መጋለጣቸውንም ድርጅቱ የጠቆመ ሲሆን የኦሮሚያ ጤና ቢሮም በሽታውን ለመቆጣጠር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል ።