በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪካን አይታ የማታውቀው ቸነፈር የገጠማት ለምንድነው?


አፍሪካን አይታ የማታውቀው ቸነፈር የገጠማት ለምንድነው?
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:26 0:00

አፍሪካን አይታ የማታውቀው ቸነፈር የገጠማት ለምንድነው?

አፍሪካ እስከዛሬ አይታ የማታውቀው የምግብ ቀውስ ገጥሟታል። ዲፕሎማቶችም ቀውሱ ግዙፍና ውስብስብ መሆኑን እያሳሰቡ ነው፡፡ ሁኔታው ባለፈው አንድ ዓመት መባባሱን በመግለጽ፣ ግጭትና የአየር ንብረት ለውጥ ዋነኛውም ምክንያት መሆኑን ይናገራሉ፡፡

ናዲፋ አብዲ ኢሳክ በምግብ እጦት እጅግ የተጎዱትን ሴቶች ልጆቿን ሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ ወደሚገኝ ሆስፒታል ለማምጣት ተገዳለች።

ናዲፋና ቤተሰቧ የሚኖሩበትን ከተማ ከመታው ድርቅና ቸነፈር ለማምለጥ ተስፋ በማድረግ ወደ ሞቃዲሾ የመጡት በእግራቸው ሲሆን 12 ቀናት ፈጅቶባቸዋል።

ከልጆቿ ሶስቱ የደም ማነስ ያለባቸው መሆኑን በመግለጽ በአስቸኳይ ደም ሊሰጣቸው እንደሚገባም ናዲፋ ተናግራለች።

ናዲፋ ሆስፒታል በደረሰችበት ቀን 42 የሚሆኑ ሕጻናት በረሃብ ተጎድተው እንደገቡ፤ ቀደም ባለውም ቀን 57 ህጻናት እንዲሁ መግባታቸውን በሆስፒታሉ የምታገለግለው ነርስ አስታውቃለች።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደሚለው በሶማሊያ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ ሕጻናት ከቸነፈር ጋር ተፋጠዋል። ይህ ከየትኛውም የዓለም ክፍል ከሚገኝ አሃዝ ትልቁ ነው።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከአምስት አፍሪካውያን አንዱ፣ ማለትም 278 ሚሊዮን የሚሆኑ አፍሪካውያን ካለፈው ዓመት ጀምሮ የተራቡ መሆኑን ገልጾ፣ ዋናው ችግር ግን ገና እየመጣ ነው ሲል ያስጠነቅቃል።

በምሥራቅ አፍሪካ አራት የዝናብ ወቅቶች ደረቅ ሆነው አልፈዋል። ይህ በአሥርት ዓመታት ውስጥ ያልታየ ነው ተብሏል።

በሌላኛው የአህጉሪቱ ጫፍ፣ በምዕራብ አፍሪካ ግን ታይቶ የማይታወቅ ዝናብ እየጣለ ሲሆን አካባቢውም በጎርፍ ተጥለቅልቋል።

ከኮቪድ 19 ወረርሽን ወዲህ አፍሪካ የገባችበት ከባድ የዕዳ መጠን የህዝቡን ኑሮ እያናጋው ነው። የዋጋ ማሻቀብና በዩክሬን ያለው ጦርነትም ሁኔታዎችን ማባባሱ ተመልክቷል፡፡

የሕጻናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) የቀጠና ሃላፊ የሆኑት ራኒያ ዳጋሽ “በአሁኑ ወቅት በሶማሊያም ሆነ በአፍሪካ ቀንድ ያለው ችግር የአየር ንብረት ለውጥ ያስከተለው ቀውስ ነው። ድርቅ ነው።” ያላሉ፡፡ ይሁን እንጂ ግን “በዩክሬን ባለው ጦርነት ምክንያት የምግብ፣ የነዳጅም ሆነ የሌሎች ሸቀጦች ዋጋ በጣም በመጨመሩ፣ የሚያስፈልገንን ለማግኘት ተጨማሪ ገንዘብ ያስፈልገናል።” ሲሉም ይማጸናሉ፡፡

በአፍሪካ ግጭቶች በመባባስ ላይ መሆናቸው ይነገራል፡፡ ግጭቶች ሁሌም ሰዎችን ከመኖሪያቸውና ከአርሻቸው በማፈናቀል ረሃብን ያስከትላሉ፣ ለዕርዳታዎች ተደራሽነትም ጋሬጣ ይሆናሉ።

ተመድ እንደሚለው በአፍሪካ የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር፣ ከዚህ በፊት ታይቶ በማያውቅ ደረጃ፣ በተገባደደው የአውሮፓውያን ዓመት 36 ሚሊዮን ደርሷል።

ይህ ቁጥር በዓለም ከተፈናቀሉት አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ግማሽ ያህል መሆኑ ተመልክቷል።

XS
SM
MD
LG