በሽረ፣በአላማጣ እና በኮረም ከተሞች የተወሰኑ የባንክ አገልግሎቶችን መጀመሩን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ፡፡ አንዳንድየግል ባንኮችም በእነዚህ ከተሞች የተወሰነ የባንክ አገልግሎት መስጠት እንደጀመሩ ሲገለጽ የተጀመረው አገልግሎት ከሌላ አካባቢየተላከን ገንዘብ መቀበልና ብር ማስገባት ብቻ እንደሆነ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡
ቅርንጫፍ ባንኮቹ ሙሉ አገልግሎት የማይሰጡበት ምክንያት መረጃ ለማስተላለፍ የሚያስችል ኢንተርኔት ስለሌለና የብር እጥረትም ስላለባቸው እንደሆነ አንድ የባንክ ባለሙያ ተናግረዋል፡፡