በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኤርትራ ሥልጠና ላይ የነበሩ የሶማሊያ ወታደሮች ወደ ሀገራቸው ሊመለሱ ነው


ፎቶ ፋይል የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሃሳን ሼክ ሞሃመድ ዓርብ ኅዳር 2 /2015 ዓ.ም ኤርትራን በጎበኙበት ወቅት ፕሬዚዳንቱ በኤርትራ አየር ኃይል በመሰልጠን ላይ ይሚገኙ የሶማልያ ወታደሮች አነጋግረው ነበር።
ፎቶ ፋይል የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሃሳን ሼክ ሞሃመድ ዓርብ ኅዳር 2 /2015 ዓ.ም ኤርትራን በጎበኙበት ወቅት ፕሬዚዳንቱ በኤርትራ አየር ኃይል በመሰልጠን ላይ ይሚገኙ የሶማልያ ወታደሮች አነጋግረው ነበር።

በኤርትራ ሥልጠና ላይ የነበሩ የሶማሊያ ወታደሮች በዚህ ወር ወደ ሀገራቸው መመለስ እንደሚጀምሩ የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ትናንት አስታወቁ። ለስልጠና ኤርትራ የነበሩት የሶማሊያ ወታደሮች በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ሳይሳተፊ አይቀርም የሚል ወሬ ለወራት ሲሽከረከር ቆይቷል።

አሜሪካ በጉብኝት ላይ የሚገኙት የሶማሊያው ፕሬዚደንት ሃሰን ሼክ ሞሃመድ ከሀገራቸው ተወላጆች ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ከዚህ የአውሮፓውያኑ ወር መጨርሻ ጀምሮ ወታደሮቹ መመለስ እንደሚጀምሩና በሚቀጥለው ወር ተጠናቀው እንደሚገቡ ተናግረዋል።

የፕሬዚደንቱ ንግግር በሀገራቸው የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ተሰራጭቷል።በምርጫ ዘመቻ ወቅት ወታደሮቹን ወደ አገራቸው ለመመለስ ቃል ገብተው የነበሩት ሼክ ሞሃመድ፣ ባለፈው ሐምሌ ወደ ኤርትራ በመጓዝ ጎብኝተዋቸው ነበር።

በሠራዊቱ ውስጥ ያሉ ልጆቻቸው የት እንዳሉ የማያውቁ ቤተሰቦች ባለፈው ዓመት ተቃውሞ ሲያሰሙ እንደነበር ይታወሳል። በወቅቱ የአገሪቱ ፕሬዝደንት የነበሩትን ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ ወይም ፎርማጆን ሲስያስጨንቁ ከርመዋል።

በኤርትራ ያለውን የሰብዓዊ ሁኔታ በተመለከተ የተመድ ልዩ ራፖርተር የሆኑት ሞሃመድ አብደልሰላም ባቢከር፣ የኢትዮጵያን ሃይሎች ለማገዝ “የሶማሊያ ወታደሮች ከኤርትራ ወታደሮች ጋር በመሆን ከማሰለጠኛ ካምፖች ወደ ትግራይ ግንባር ተልከዋል የሚሉ ሪፖርቶች” መኖራቸውን ባለፈው ሰኔ ጠቁመዋል።

መንግስታቸው 5 ሺህ የሚሆኑ ወታደሮችን ለስልጠና ወደ ኤርትራ መላኩን ፎርማጆ ባለፈው ግንቦት አስታውቀው ነበር። ስልጠናቸው ማለቁን ነገር ግን የፓርላማ እና የፕሬዝደንታዊውን ምርጫ ላለማስተጓጎል የመመለሳቸውን ጉዳይ እንዳዘገዩት ፎርማጆ በወቅቱ አስታውቀው ነበር።

XS
SM
MD
LG