No media source currently available
በሀገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ላይ ካገለገሉ ጥቂት ኢትዮጵያዊያን ዳኞች መካከል አንዷ ጌራ ወርቅ ከተማ ናት ። በአሁኑ ሰዓት በጨዋታ ታዛቢነት (ኮሚሽነርነት ) እያገለገለች ያለችው ጌራ ወርቅ ፣ ሴት የእግር ኳስ ዳኞች እንዲበራከቱ ተጨማሪ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው ትናገራለች ። የዓለም ዋንጫን አስታከን በእንግድነት የጋበዝናት ጌራወርቅ ፣ ስለሙያዊ ጉዞዋ እና ተያያዥ ጉዳዮች ሀሳቦቿን ታጋራናለች ።