በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፕሬዚደንት ባይደንና የአፍሪካ መሪዎች የጋራ ፎቶግራፍ ስነ-ስርዓት


የፕሬዚደንት ባይደንና የአፍሪካ መሪዎች የጋራ ፎቶግራፍ ስነ-ስርዓት
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:44 0:00

የፕሬዝደንት ባይደንና የአፍሪካ መሪዎች የጋራ ፎቶግራፍ ስነ-ስርዓት

ለሦስት ቀናት የተካሄደው የዩኤስ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ትናንት ሐሙስ ሲጠናቀቅ ፕሬዚደንት ጆ ባይደንናተጋባዥ የአፍሪካ ሃገሮች መሪዎች በጋራ ፎቶ ተነስተዋል።

ከሰሃራ ግርጌ ወዳሉ የአፍሪካ አገሮች በቅርቡ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ፕሬዚደንት ባይደን በጉባኤው ላይ አስታውቀዋል። እድገት እያስመዘገበወዳለው አህጉር አሜሪካ ትኩረቷን እንደምትጨምርም ጠቁመዋል።

ከፍተኛ አማካሪዎቻቸውን ወደ አፍሪካ እንደሚልኩ፣ ከእነዚህም ውስጥ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንተኒ ብሊንከን፣ የገንዘብ ሚኒስትሯ ጃነት የሊን እና የንግድ ሚኒስትሯ ጂና ሬይሞንዶ እንደሚገኙበት ባይደን አስታውቀዋል።

ባይደን ከሰሃራ ግርጌ ወዳሉ የአፍሪካ አገሮች የሚያደርግት ጉብኝት እንደ ፕሬዝደንት የመጀመሪያው ነው። ባለፈው ኅዳር የዓለም የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ በግብጽ የአጭር ግዜ ቆይታ አድርገው ነበር።

ፕሬዚደንቱ ከሰሃራ በታች ወዳሉ የአፍሪካ አገሮች የሚያደርጉት ጉዞ መቼ እንደሆነና የትኞቹን አገሮች እንደሚጎበኙ አላስታወቁም።

ባይደን በመጀመሪያው የሁለት ዓመት የሥልጣን ዘመናቸው ወደ ውጪ የሚያደርጉትን ጉዞ በአውሮፓና በእሲያ ላይ እንዲያተርኩር አድርገዋል። ይህም የውጪ ፖሊሲያቸው በዚያ አካባቢ ላይ እንዲያተኩር በመፈለጋቸው ነው

ተብሏል። በመጀመሪያው የሁለት ዓመት የሥልጣን ዘመናቸው ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈጸመችው ወረራ ያስከተለውን ዳፋ ተጋፍጠዋል።

ከባይደን በፊት የነበሩት ሪፐብሊካኑ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ባጠላበት የሥልጣን ዘመናቸው፣ ወደ አፍሪካ ጉዞ አላደረጉም። በመጨረሻዎቹ 11 ወራት የስልጣን ጊዜያቸው ጭራሽ ወደ ውጪ ጉዞ አላደረጉም።

ባይደን ትናንት ሐሙስ በአፍሪካ በሚቀጥለው ዓመት ለሚደረጉ ምርጫዎች 165 ሚሊዮን ዶላር እንደሚመደብ ቃል ገብተዋል። ይህም ምርጫን ተከትሎ ሁከት በሚያጠቃቸው አንዳንድ አገሮች ሰላማዊ፣ አስተማማኝና ፍትሃዊ ምርጫ እንዲደረግ ለማስቻል የሚውል ነው ተብሏል።

የትናንቱ ወይይት ያተኮረው የአፍሪካ ኅብረት ለአህጉሪቱ በያዘው ራዕይ ላይ ነበር። ከዚህም ውስጥ የምግብ ዋስትና ጉዳይ አንዱ ነው።

በዓለም በተለይም ሩሲያ በዩክሬን ላይ ከፈጸመችው ወረራ ወዲህ እየጨመረ በመጣው የምግብ ዋጋ አፍሪካ ይበልጥ ተጎጂ ሆናለች።

ቡድን 20 እየተባለ የሚጠራውና በዓለም በኢንዱስትሪና በኢኮኖሚ የበለጸጉ አገሮች አባል የሆኑበት ማኅበር ውስጥ የአፍሪካ ኅብረትም አባል እንዲሆን ባይደን ድጋፋቸውን እንደሚሰጡ ዋይት ሃውስ ባለፈው ሳምንት አስታውቆ ነበር። የቡድን 20 ውስጥ ዓባል የሆኑት አገሮች ከዓለም አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት 80 በመቶውን ይሸፍናሉ። ከአፍሪካ እስከ አሁን በቡድን 20 ውስጥ

አባል የሆነቸው አገር ደቡብ አፍሪካ ብቻ ነች። የአፍሪካ ኅብረት ደግሞ 54 አገሮችን የሚወክል ነው።

በጤና፣ መሠረተ ልማት፣ ንግድ እና ቴክኖሎጂ መስክ አህጉሪቱ እመርታ እንድታሳይ ከአሜሪካ መንግስት በሚመደብና በግሉ ዘርፍ በሚከናወን መዋዕለ-ንዋይ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ እንደተመደበ ባይደን ባለፈው ረቡዕ ይፋ አድርገዋል።

ፕሬዚደንት ባይደንና ባለቤታቸው ጂል ባይደን የአፍሪካ አገራት መሪዎችንና ቀዳማዊ እመቤቶቻቸውን በዋይት ሃውስ የእራት ግብዣ አድርገውላቸዋል።

XS
SM
MD
LG