በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን ሚሳይሎች ለመላክ ያላት ዕቅድ “ጸብ አጫሪነት” ነው ስትል ሩሲያ አስጠነቀቀች


ኬኼርሶን
ኬኼርሶን

ዩክሬን ዛሬ ሩስያ በደቡቧ ኬኸርሳን ከተማ በፈጸመችው የመድፍ ድብደባ ሁለት ሰዎች ገድላለች ስትል ተናገረች፡፡ በሌላ በኩል ሩሲያ የዩክሬን ምስራቃዊ ከተማ ዶኔትስክ ያስቀመጠቻቸው ባለስልጣናት በበኩላቸው የዩክሬን ኅይሎች ጥቃት አድርሰዋል ሲሉ ከስሰዋል፡፡

ይህ በእንዲህ አንዳለ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ቮልከር ቱርክ በሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤቱ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር “ሩስያ ዩክሬን ላይ የከፈተችውን ጦርነት ከባድ የዐለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ህግጋት ጥሰት በመፈጸም ገፍታበታለች” ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት ዩክሬንን የጎበኙት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነሩ 18 ሚሊዮን ዩክሬናውያን ሰብዓዊ ዕርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው አመልክተዋል፡፡ አያይዘውም ሩሲያ ዓየር ድብደባዋን ከቀጠለች ሰብዓዊ ችግሩ አንደሚባባስ እና የተፈናቃዮች ቁጥር እንደሚያሻቅብ አሳስበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG