በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬን13 የሩሲያ ሰው አልባ ጢያራዎችን ጣልኩ አለች


የወደቁ ሩሲያ ድሮኖች
የወደቁ ሩሲያ ድሮኖች

ረቡዕ ዕለት የዩክሬን ባለስልጣናት ሩሲያ ኢራን ሰራሽ በሆኑ ሰው አልባ ጢያራዎችን በመጠቀም የዩሬን ዋን ከተማ ኪየቭን ማጥቃቷን ያስታወቁ ሲሆን በጥቃቱ ሁለት የመንግስት ህንጻዎች መጎዳታቸው ተገልጿል።

የኪየቭ ከንቲባ ቪታሊ ክሊችኮ በማዕከላዊ ኪየቭ በሚገኘው የሼቭቼንኪቭስኪ ወረዳ ፍንዳታ ደረሰ ያሉ ሲሆን፤ እስካሁን ድረስ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት ካለ አልተገለጸም።

የዩክሬን ጦር ሩሲያ የተለያዩ ከተሞቼን ለማውደም የተጠቀመቻቸውን ዓይነት ተመሳሳይ 13 ሰው አልባ ጢያራዎችን ጥያለሁ ብሏል።

የዩክሬን መከላከያ ሚንስትር “ኪየቭ ላይ ሌላ ግዙፍ የጢያራ ድብደባ ተፈጽሞባታል። ሩሲያ ሰላማዊ ከተሞችን ስትደበድብ ብቻ ወታደራዊ በራስ መተማመን እንደሚኖራት ግልጽ ነው” ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

የአውሮፓ ህብረት ሩሲያ በዩክሬን ውስጥ በምታደርገው ጦርነት የምትጠቀመውን ሰው አልባ አውሮፕላኖች በማዘጋጀት እና በማቅረብ ላይ ባላት ሚና የተነሳ በዚህ ሳምንት በኢራን ላይ ማዕቀብ ጥሏል።

በሌላ በኩል የጣሊያን ወታደሮች በቡልጋሪያ ኖቮ ሴሎ የኔቶ ተዋጊ ቡድንን እየመሩ ሲሆን የመልሶ ማጥቃት ወታደራዊ ልምምድ በማድረግ ሳሉ የሚያዩ ምስሎች በትላንትናው ዕለት ተጋርተዋል።

XS
SM
MD
LG