በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፌስቡክ በኢትዮጵያ ጥቃት በሚያነሳሱ ጹሑፎች ይዘት ምክኒያት ክስ ተመሰረተበት 


META-ETHIOPIA
META-ETHIOPIA

ኢንስታግራም፣ ፌስቡክንና ዋትስአፕን የሚያስተዳድረው ሜታ ኩባንያ በኢትዮጵያ ጥቃት የሚያነሳሱ የጥላቻ መልዕክቶች በገፁ ላይ እንዲሰራጭ በማድረግ ደም አፋሳሽ የሆነ የእርስ በርስ ጦርነት እንዲባባስ አድርጓል በሚል ክስ ተመሰረተበት።

ትላንት ኬንያ ውስጥ ክሱን የመሰረቱት ሁለት ኢትዮጵያውያን ተመራማሪዎች እና ካቲባ ኢንስቲቲዩት የተባለው የኬኒያ የመብቶች ተቋም መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።ከሳሾቹ ሜታ ኩባኒያ ፌስቡክ ላይ በወጡ መልዕክቶች ሳቢያ ጥቃት ለደረሰባቸው ሰለባዎች ካሳ የሚውል 2 ቢሊዮን ዶላር ካሳ እንዲመድብ ጠይቀዋል።

ፌስቡክ በገጹ ላይ የሚሰራጩ መልዕክቶችን በኢትዮጵያ ጥቃት እንዲጨምር አባብሰዋል የሚል ክስ የቀረበበት ድርጅቱ ከክስ መስራቹቹ አንዱ አባቱ ከመገደላቸው አስቀድሞ አስቀድሞ እንዲህ ያሉ ይዘቶች ያሏቸው ብዙ መልዕክቶች ፌስቡክ ላይ ሲስተጋቡ እንደነበር አመልክቷል።

በተጨማሪም ፊስቡክ አደገኛ መልዕክቶችን ለመለየት የሚያስችሉ አልጎሪዝሞችን ወይም የአሠራር ሥርዓት ቀመር በሚመለከት ለሠራተኞቹ በቂ ስልጠና ባለመስጠትና ናይሮቢ የሚገኘው የመልዕክቶች ይዘት ቁጥጥር ማዕከሉ ለሚከታተላቸው ቋንቋዎች በቂ ሠራተኛ ባለመቅጠርም ክስ ቀርቦበታል።

ጥቃት ቀስቃሽ መልዕክቶችን የሚያወርዱ አስቸኳይ እርምጃዎች እንዲወስድና ለናይሮቢው የይዘት ቁጥጥር ማዕከሉ ተጨማሪ ሠራተኞች እንዲቀጥር በፍርድ ቤት እንዲታዘዝ ክስ መስራቹቹ ጠይቀዋል።

የሜታ ቃል አቀባይ ኤሪን ሜክፓይክ በበኩላቸው የጥላቻ ንግግርና ጥቃት መቀስቀስ ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በሚመሩባቸው ደንቦች ተቀባይነት የላቸውም ብለዋል።

“እንዲህ ዐይነት ይዘት ያላቸውን መልዕክቶች ተከታትለው በሚያስወግዱ ባለሞያዎችና ቴክኖሎጂ ላይ ኩባኒያችን መጠነ ሰፊ መዋዕለ ነዋይ ያፈሳል” ያሉት የሜታ ቃል አቀባይ “የምንቀጥረው ስለሀገሩ የሚያውቁ ባለሞያዎች ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ስፋት በሚነገሩ ቋንቋዎች የሚወጡ የፊስቡክን ደንቦች የሚጥሱ ይዘቶች ተከታትሎ የማስወገድ አቅማችንን ለማሳደግ ጥረታችንን እንቀጥላለን” ብለዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ግጭት የሚያባብሱ ይዘት ያላቸው መላክቶችን ለማሰራጨት ፌስቡክና ኢንስታግራም እንዴት ጥቅም ላይ እንደዋሉ ምርመራ እንዲካሄድ ባለፈው ዓመት የሜታ ነጻ ተቆጣጣሪ ቦርድ ምክረ ሃሳብ መስጠቱ ይታወሳል።

በአውሮፓውያኑ የቀን አቆጣጥር በ2021ዓም ጥቅምት ወር ላይ የአብርሃም አባት ብሄር ላይ ያነጣጠረ ስድብና ዘለፋ የያዘ ጹሑፍ ተሰራጭቶ እንደነበር ፤ ከጹሑፉም ጋር አድራሻቸው ተያይዞ “ይገደሉ” የሚል ጥሪም ቀርቦበት እንደነበር በክሱ ዶሴ ተዘርዝሯል። አብርሃም ለፌስቡክ አቤቱታ ቢያቀርቡም ኩባኒያው መልዕክቶቹን ፈጥኖ ለማስወገድ ፈቃደኛ እንዳልነበረ እና አንዳንዶቹን መልዕክቶች ፈጽሞ እንዳላስወገዳቸው በቀረበው ክስ ተዘርዝሯል።

XS
SM
MD
LG