በአፍሪካ በአሁኑ ወቅት ያሉ ዋና ዋና ችግሮችን መፍትሄ ለመስጠት ዩናይትድ ስቴትስ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር እንደምታወጣ የሃገሪቱ የብሄራዊ ፀጥታ አማካሪ ጄክ ሰለቫን ዛሬ አስታውቀዋል።
በሌላ በኩል የዩናይትድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ከአፍሪካ የንግድና የፈጣራ ሰዎች ጋር ትናንት ማምሻውን መሥሪያ ቤታቸው ውስጥ ባደረጉት ስብሰባ “ከአፍሪካ ጋር መኖር አለበት” ስላሉት ትብብር አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል። /ዘገባው ከሮይተርስና ከአሶስዬትድ ፕረስ የተወሰደ ነው/