በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፈረንሳይ በዩክሬን  እርዳታ ላይ ለመነጋገር ዓለም አቀፍ ለጋሾችን ሰብስባለች

French President Emmanuel Macron (C) greets Ukrainian Prime Minister Denys Shmyhal (L) as he arrives at the presidential Elysee Palace, in Paris, on Dec. 13, 2022.
French President Emmanuel Macron (C) greets Ukrainian Prime Minister Denys Shmyhal (L) as he arrives at the presidential Elysee Palace, in Paris, on Dec. 13, 2022.

ዩክሬን መሰረተ ልማት አውታሮቿ ላይ በሩሲያ የሚፈፀምባትን ጥቃት እንድትቋቋም መርዳት በሚቻልበት መንገድ ላይ ያተኮረ ጉባዔ ዛሬ ማክሰኞ ተከፍቷል። ጉባዔውን የጠራችው የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ኢማኑዌል ማክሮን የዩክሬን ህዝብ ክረምቱን እንዲወጣ ለመርዳት የታለመ ጉባዔ መሆኑን አስታውቀዋል።

የዩክሬን ፕሬዚደንት ቮሎዶሚር ዘሌንስኪ ለጉባዔው በኢንተርኔት አማካይነት ባደረጉት ንግግር "ሀገራችን ለወታደሮቿ ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎች እንደሚያስፈልጓት ሁሉ በዚያው ደረጃ የኤሌክትሪክ ጄኔሬተሮችም ያስፈልጉናል" ሲሉ የጉባዔውን ተሳታፊዎች አሳስበዋል።

የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚደንት ኡርሱላ ቮን ደር ሊየን በበኩላቸው የአውሮፓ ኅብረት ለዩክሬን ሆስፒታሎች የሚውሉ 40 ጄኔሬተሮችን እንዲሁም ለሌሎች የሀገሪቱ ተቋማት 800 ጄኔሬተሮች እንደሚልክ አስታውቋል።

ትናንት ሰኞ የቡድን ሰባት አባል ሀገሮች መሪዎች ዩክሬን በአፋጣኝ የሚያስፈልጋትን ወታደራዊ እና የመከላከያ ቁሳቁስ ድጋፍ ለማሟላት ቃል ገብተዋል።

XS
SM
MD
LG