በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩኤስ-አፍሪካ መሪዎች ጉባዔ በመጭው ሣምንት ይካሄዳል


የዩኤስ-አፍሪካ መሪዎች ጉባዔ በመጭው ሣምንት ይካሄዳል
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:27 0:00

የዩኤስ-አፍሪካ መሪዎች ጉባዔ በመጭው ሣምንት ይካሄዳል

በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የተጠራ የዩናይትድ ስቴትስ-አፍሪካ መሪዎች ጉባዔ ከፊታችን ማክሰኞ፤ ታኅሣስ 4 እስከ ሃሙስ፤ ታኅሳስ 5 / 2015 ዓ.ም. ዋሺንግተን ዲ.ሲ. ውስጥ እንደሚካሄድ ታውቋል።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አስተናባሪነት በተዘጋጀና ትናንት፤ ረቡዕ ምሽት በተካሄደ የኢንተርኔት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተናገሩ ሁለት የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መሪዎቹ በዋሺንግተን ቆይታቸው ወቅት በአንገብጋቢ ዓለም አቀፍና የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ እንደሚነጋገሩ አመልክተዋል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ የ49 ሀገሮች መሪዎች የተጋበዙ ሲሆን ኤርትራ፣ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሌላቸው፣ እንዲሁም ሱዳንና ሌሎችም ሥልጣን በመፈንቅለ መንግሥት የያዙ መሪዎች ያሉባቸው ጥቂት ሃገሮች ከግብዣው ውጭ ተደርገዋል።

XS
SM
MD
LG