በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሽረ ከተማ ኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘት መጀመሯ ተገለፀ


ሽረ ከተማ ኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘት መጀመሯ ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:45 0:00

ሽረ ከተማ ኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘት መጀመሯ ተገለፀ

ሽረ ከተማ የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘት መጀመርሯን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል፡፡ አቶ ሞገስ "ከተከዜ ግድብ ወደ ሽረ ከተማ የሚሔደው የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ጥገና ዛሬ በመጠናቀቁ ለከተማዋ ኃይል ማቅረብ ተችሏል" ብለዋል።

የሽረ ከተማ ኃይል ማግኘት በአካባቢው የሚገኙ ሌሎች ከተሞችንም ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡ ከሰሞኑ የመቐለ ከተማ ከዋናው ብሔራዊ የኃይል ቋት ጋር በመገናኘቷ፣ ከዚሁ ሀገራዊ መስመር ሀይል እንደምታገኝ የገለፁት አቶ ሞገስ፣ እስከ መቐለ ድረስ ያሉት ከተሞችም የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘት መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG