በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፀረ አፓርታይድ ታጋዩን የገደለው እስረኛ መለቀቅ ተቃውሞ ቀሰቀሰ


ፀረ አፓርታይድ ታጋዩን የገደለው እስረኛ መለቀቅ ተቃውሞ ቀሰቀሰ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:25 0:00

ፀረ አፓርታይድ ታጋዩን የገደለው እስረኛ መለቀቅ ተቃውሞ ቀሰቀሰ

ፀረ አፓርታይድ ታጋዩን ደቡብ አፍሪካዊ ክሪስ ሃኒን የገደለው ያኑሽ ዋሉስ ከ28 ዓመታት በኋላ ከእስር መለቀቁ ተቃውሞ ቀስቅሷል። የ69 ዓመቱ ዋሉስ በአመክሮ እንዲፈታ ከተወሰነ በኋላ ትላንት ረቡዕ ክእስር ቤቱ ሆስፒታል ተለቋል፡፡

ዋለስ ባለፈው ሳምንት መለቀቅ እንደነበረበት የገለፁት የፍትሕና ማረሚያ አገልግሎት ሚኒስትር ሮናልድ ላሞላ ከእስር ከመለቀቁ ሁለት ቀናት አስቀድሞ እስረኛ በስለት መወጋቱን ተናግረዋል፡፡

ያኑሽ ዋለስ የተለቀቀው ከዚህ ቀደም የፍትሕ ሚኒስትሩ በአመክሮ እንዳይለቀቅ የሰጡት ውሳኔ “ምክንያታዊ አይደለም” በሚል በፍርድ ቤት ውድቅ ከተደረገ በኋላ መሆኑ ታውቋል።

ደቡብ አፍሪካዊው ካሌቡ ማቴምቡ “ይሄ ደስ የሚል ነገር አይደለም ምክንያቱም መለቀቅ አልነበረበትም፡፡ አርማችን የሆነውን መሪያችንን የገደለ ስለሆነ እስር ቤት መበስበስ ነበረበት፡፡" ብለዋል።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG