በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ አሜሪካዊቷን እስረኛ ብርትኒ ግራይነር በልውውጥ ለቀቀች

ፋይል - አሜሪካዊቷ የሴቶች ቅርጫት ኳስ ኮከብ ብርትኒ ግራይነር እ.አ.አ በ2020 በጃፓን ተካሂዶ በነበረው የበጋ ኦሎምፒክስ የወርቅ ሜዳሊያ ጨዋታ ላይ ስትጫወት ትታያለች።
ፋይል - አሜሪካዊቷ የሴቶች ቅርጫት ኳስ ኮከብ ብርትኒ ግራይነር እ.አ.አ በ2020 በጃፓን ተካሂዶ በነበረው የበጋ ኦሎምፒክስ የወርቅ ሜዳሊያ ጨዋታ ላይ ስትጫወት ትታያለች።

በሩሲያ ታስራ የነበረችው አሜሪካዊቷ የሴቶች ቅርጫት ኳስ ኮከብ ብርትኒ ግራይነር በእስረኛ ልውውጥ መለቀቋን አንድ የአሜሪካ ባለስልጣን አስታውቀዋል።

አሜሪካ በበኩሏ ሩሲያዊውን የመሣሪያ ሺያጭ ቪክተር ባውት በምትኩ ለቃለች።

“ከብርትኒ ጋር በስልክ ተነጋግሪያለሁ፣ ደህንነቷም የተጠበቀና ወደ ሃገሯም በመብረር ላይ ነች” ሲሉ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በትዊተር አስታውቀዋል።

የሁለት ግዜ የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆነችው ብርትኒ ግራይነር የካናቢስ ዘይት ይዘሻል በሚል ባለፈው የካቲት በሞስኮ አየር ማረፊያ መያዟ ይታወሳል።

አደንዛዥ ዕፅ በሕገ-ወጥ መንገድ በማስገባት በሚል በሞስኮ የሚገኝ ፍ/ቤት ከ4 እስከ 9 ዓመት በሚደርስ እስራት ቀጥቷት ነበር።

XS
SM
MD
LG