በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የዩክሬኑን ጦርነት ከናዚ ዘመቻ ጋር አመሳሰሉ


ፋይል - ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዩክሬን ጉዳይ ንግግር ሲያደርጉ
ፋይል - ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዩክሬን ጉዳይ ንግግር ሲያደርጉ

የካቶሊኩ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዩክሬን እየተካሄደ ያለውን ሁኔታ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ከተፈጸመውና 2 ሚሊዮን አይሁዶች ከተገደሉበት የናዚ ዘመቻ ጋር አመሳስለውታል።

ከፖላንድ ለመጡ መንፈሳዊ ተጓዦች ንግግር ያደርጉት ሊቀ ጳጳሳት ፍራንሲስ “ዘመቻ ሬንሃርድ” ተብሎ የሚጠራውንና በጀርመን ተይዛ በነበረችው ፖላንድ እና የተወሰነ የዩክሬን ክፍል ውስጥ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ አስታውሠዋል።

“ታሪክ ራሱን ይደግማል፣ በዩክሬን እየሆነ ያለውን እያየን ነው” ብለዋል ጳጳሱ በንባብ እያቀረቡ የነበሩትን ንግግር አቋርጠው።

በ”ዘመቻ ሬንሃርድ” ከእ.አ.አ ከ 1941 እስከ 1943 ባለው ግዜ ውስጥ ጀርመኖቹ ሶስት የግድያ ማዕከላት እንዳቋቋሙ የዩናይትድ ስቴትስ ሆሎካስት ሙዚየም ድህረ ገጽ ይገልጻል።

ሩሲያ በዩክሬን እያደረገች ያለውን እንቅስቃሴ “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” ብላ ስትጠራው፣ ይህም አገሪቱን “ከናዚ ለማጽዳት” ነው ብላለች።

ዩክሬንና አጋሮቿ ደግሞ የሩሲያ ተግባር የምዕራቡ አጋር ከሆነችው አገር ላይ ግዛት ለመንጠቅ ነው ይላሉ።

የሩሲያ ወረራ ከጀመረ አንስቶ ጳጳስ ፍራንሲስ ድርጊቱን ሲኮንኑ ሰንብተዋል።

ባለፈው ወር ባደረጉት አንድ ንግግር ላይ፣ በዩክሬን ያለውን ሁኔታ “ዘግናኝ የዘር ማጥፋት” ብለው ከጠሩትና እ.አ.አ በ1930ዎቹ የወቅቱ የሶቪዬት ኅብረት መሪ ጆሴፍ ስታሊን አገሪቱን በረሃብ ከቀጣበት ወቅት ጋር አመሳስለውታል።

ጳጳሱ ግጭቱን ቫቲካን እንድትሸመግል በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ በሩሲያ ላይ ያላቸው ብርቱ ነቀፌታ ግን አሸማጋይ የመሆናቸውን ዕድል አጥብቦታል።

XS
SM
MD
LG