በኳታር የዓለም ዋንጫ በመጨረሻው 16 ፍፁም ቅጣት ምት ስፔንን ያሸነፈችው ሞሮኮ ደጋፊዎች ትላንት በሊል ከተማ ከፈረንሳይ ፖሊሶች ጋር ተጋጭተዋል። ሮይተርስ ያወጣው ምስል ደጋፊዎች እሳት ሲያቀጣጥሉ እና ርችት ሲተኩሱ እና አድማ በታኝ ፖሊሶች ሁኔታውን ለመቆጣጠር ሲሯሯጡ ያሳያል። ሞሮኮ ትላንት ማክሰኞ ለመጀመሪያ ግዜ በአረብ ሀገር በተዘጋጀው የወንዶች ዓለም ዋንጫ ስፔንን በማሸነፍ እና ተፎካካሪዎቿን ከውድድር ውጪ በማድረግ በኳታር ሩብ ፍፃሜ ለመድረስ የቻለች የመጀመሪያዋ አረብኛ ተናጋሪ ሀገር ሆናለች።
በማክሰኞው ጨዋታ ሞሮኮ እና ስፔን በሙሉ እና በተጨማሪ ሰዓት ካለምንም ግብ ከተለያዩ በኃላ በተሰጠው የፍፁም ቅጣት መለያ በአጠቃላይ ውጤት ሞሮኮ 3-0 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።
(ሮይተርስ)