በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምስራቅ ወለጋ ዞን በኮማንድ ፖስት እንዲተዳደር ሦስት ፓርቲዎች ጠየቁ


ምስራቅ ወለጋ ዞን በኮማንድ ፖስት እንዲተዳደር ሦስት ፓርቲዎች ጠየቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:58 0:00

ምስራቅ ወለጋ ዞን በኮማንድ ፖስት እንዲተዳደር ሦስት ፓርቲዎች ጠየቁ

ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን በኮማንድ ፖስት ስር እንዲተዳደርና አካባቢውንም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እንዲቆጣጠረው ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠየቁ፡፡

እናት፣ ኢህአፓና መኢአድ ዛሬ በጋራ በሰጡት መግለጫ፣መንግሥት ቁጥራቸው ለበዛ ሰላማዊ ሰዎች ህልፈትና መፈናቀል ምክንያት የሆኑት ኃይሎችን ለሕግ እንዲያቀርብና በአካባቢው እየተፈፀመ ስላለው ጥቃት ለሕዝብ አስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጥ አሳስበዋል።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ /ኦፌኮ/ መንግሥት የምስራቅ ወለጋውን ጨምሮ በኦሮሚያ ያለው አለመረጋጋት በውይይት ብቻ እንዲፈታ አሳስቧል፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ /ኢዜማ/ በበኩሉ “ለግጭቱ መሰረታዊ ችግር የሆነውን የብሔር ፖለቲካን ማስወገድ መፍትኄ ነው” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

/ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG