በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራን ከእስራኤል የስለላ ተቋም ሞሳድ ጋር ተባብረዋል ያለቻቸውን አራት ሰዎች ገደለች


ኢራን
ኢራን

የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ የዘመናት ጠላቱ የሆነችውን እስራኤልን በግዛቴ ላይ ሚስጥራዊ ተልዕኮዎችን ተፈጽማለች በማለት ስትከስ ቆይታለች። በጎርጎሮሳዊያኑ 1979 ከተካሄደው የእስልምና አብዮት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሃገሪቱን እየናጣት በሚገኘው ጸረ-መንግስት እንቅስቃሴ ጋር ተያየዞ ኢራን እስራኤል እና ምዕራባዊ የደህነት ተቋማት በሃገሬ ላይ የእርስ በርስ ጦርነት እንዲኖር እየሰሩ ነው ስትል ከሳለች።

በኢራን መንግስት የሚተዳደር መገናኛ ብዙሃን ረቡዕ እለት “ከጽዮናዊ መንግስት እና የደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር እና በጠለፋ ወንጀል” የተከሰሱ አራት ግለሰቦች ላይ የሞት ፍርድ መበየኑን ዘግቧል።

የመኸር የተሰኘ የዜና ጣቢያ ሌሎች ሦስት ሰዎች ደግሞ የሃገር ደህንነትን የሚቃረን ድርጊት በመፈጸም፣ የጠለፋ ሂደትን በማገዝ እና ህገወጥ መሳሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ከ5 እስከ 10 ዓመት የሚደርስ እስራት እንደተፈረደባቸው ዘግቧል።

የታስኒም የዜና ጣቢያ እስረኞቹ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ አሁን በሃገሪቱ እየተካሄደ ያለው አለመረጋጋት ሳይከሰት በፊት በአብዮታዊ ዘቡ እና በደህንነት ሚኒስቴ መሃከል በተደረገ ትብብር መያዛቸውን ዘግቧል።

XS
SM
MD
LG