በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

65 ከመቶ የሚሆኑ የትግራይ ኃይል ተዋጊዎች ከጦር ግንባር መገለላቸው ተገለጸ


Ethiopia-Military-Confrontation
Ethiopia-Military-Confrontation

የትግራይ ኃይሎች ዋና አዛዥ ጄነራል ታደሰ ወረደ 65 ከመቶ የሚሆኑ የትግራይ ኃይል ተዋጊዎች ከጦር ግንባር መገለላቸው አስታወቁ። ይሁን እንጂ ጄነራሉ “በአካባቢ አሁንም ድረስ ሰላም የማይሹ ኃይሎች አሉ” በማለት ኃይላቸው ይሄ ስጋት እስካልተቀረፈ ድረስ ሙሉ ለሙሉ ትጥቁን እንደማይፈታ ተናግረዋል።

እነዚህ ኃይሎች “ከባድ መሳሪያዎቻችንን በመውሰድ አንድ አካባቢ እያከማቹ ነው” ያሉት ጀነራሉ በአሁን ሰዓት በቦታው ምንም ዓይነት አለም አቀፍ ታዛቢዎች እና ተከታታዮች የሉም ሲሉ አክለዋል።

ጎርጎሮሳዊያኑ ሕዳር 02/2022 ሁለቱ አካላት ደቡብ አፍሪካ ላይ በመገኘነት ወደ ትግራይ ያልተገደበ ሰብዓዊ ድጋፍ ይገባ ዘንድ ተስማምተዋል።

በሁለት ዓመቱ ጦርነት ቁጥሩ የማይታወቅ ሰው በሞተበት በዚህ ጦርነት፤ በትግራይ እርዳታን መልሶ ተደራሽ ማድረግ ዋናው የስምምነቱ ቁልፍ ጉዳይ ነው።

የትግራይ ባለስልጣናት ማዕከላዊ መንግስቱን ሲቃወሙ ከቆዩ ከወራት በኋላ እ.ኤ.አ በ2020 ነበር የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሄ ኃይል የሃገሪቱን መከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት ፈጽሟል ሲሉ ወታደሮቻቸውን የላኩት።

በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ህውሓት እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን በሚደግፉ ከልላዊ ሚሊሺያዎች እንዲሁም በኤርትራ ሰራዊት መሃከል በተካሄደው ጦርነት እጅግ ብዙ የማይታወቅ መጠን ያለው ሞትን ያስከተለ ሲሆን ሁለት ሚሊየን የሚደርሱ ዜጎችን ለመፈናቀል በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩትን ደግሞ በርሃብ አፋፍ ላይ እንዲወድቁ አድርጓል።

ክልሉ ላለፈው አንድ ዓመት ከዓለም ጋር ተቆራርጦ የቆየ ሲሆን ከፍተኛ የሆነ የመድሃኒት እጥረት፣ የተገደበ የኤሌክትሪክ አቅርቦት እና እንዲሁም የባንክ እና የመገናኛ አገልግሎት ተደራሽነት ተግዳሮት አለበት።

XS
SM
MD
LG