በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮንጎ ብሔራዊ የሃዘን ቀን ታውጇል


የኤም-23 ተዋጊዎች በጎማ (ፎቶ ሮይተርስ)
የኤም-23 ተዋጊዎች በጎማ (ፎቶ ሮይተርስ)

በኮንጎ በስተምሥራቅ የአገሪቱ ክፍል ከመቶ በላይ ሰዎች በኤም-23 አማጽያን ተገድለዋል ካለ በኋላ መንግስት የሶስት ቀናት ብሄራዊ ሃዘን አውጇል።

መንግስት ባለፈው ሐሙስ ከጎማ 70 ኪሜ ላይ በሚገኘው ኪሺሼ በተባለ የሃገሪቱ ምሥራቅ ክፍል የኤም-23 አማጺያን 50 ሰዎችን አርደዋል ሲል ወንጅሎ ነበር።

በሩዋንዳ ይደገፋል የሚባለው ኤም-23 አማጺ ቡድን ከኮንጎ ጦር ጋር ባለፉት ወራት ከፍተኛ ግጭት ውስጥ ከርሟል።

ውንጀላው መሰረተ ቢስ ነው ያለው ኤም-23፣ ሲቪሎችን ኢላማ አላደረኩም ብሏል።

የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ፊሊክስ ቺሴኬዲ በሚኒስትሮች ስብሰንባ ላይ ሲናገሩ ከመቶ በላይ ሲቪሎች መጨፍጨፋቸውን እናወግዛለን ብለዋል።

ሲቪሎች መገደላቸው ከተሰማ በኋላ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ጥሪው ጨምሯል።

የማርች 23 ወይም ኤም-23 እየተባለ የሚጠራው ቡድን በአብዛኛው በኮንጎ ቱቲሲዎች የተዋቀረ ሲሆን፣ ለበርካታ ዓመታት ተደብቆ ከርሞ ነበር።

ባለፈው ዓመት ህዳር ወር ግን መሣሪያውን ወልውሎ እንደገና ተነስቷል። ከአንድ ወር በፊት ጥቃቱን አጠናክሮ ሰፊ ቦታዎችን ተቆጣጥሯል።

ኪንሻሳ ጎረቤት ሩዋንዳ እገዛ ትሰጣለች ስትል ትከስም፣ ኪጋሊ ታስተባብላለች።

XS
SM
MD
LG