በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢስቶኒያ የአሜሪካንን ሮኬቶች ልትገዛ ነው


(ፎቶ ኤ.ፒ)
(ፎቶ ኤ.ፒ)

የኔቶ አባልና የሩሲያ ጎረቤት የሆነችው ኢስቶኒያ ከአሜሪካ በምትገዛው የሮኬት መሣሪያዎች የመከላከያ አቅሟን ለማጠናከር እየተዘጋጀች ነው።

የኢስቶኒያ ባለሥልጣናት ዛሬ እንዳስታወቁት 200 ሚሊዮን ዶላር የሚፈጀው ግዢ አገሪቱ ከፈጸመችው የመሣሪያ ግዢዎች ሁሉ ከፍተኛው ነው።

ግዢው የሮኬት ሥርዓቶችንና ጥይቶችን እንዲሁም ስልጠናን ይጨምራል ተብሏል።

የኢስቶኒያ ጎረቤቶች የሆኑት ላቲቪያ እና ሊቱዬኒያ ተመሳሳይ ግዢ ፈጽመዋል ወይም በግዢ በሂደት ላይ ናቸው ተብሏል።

የአሜሪካው መሣሪያ አምራች ሎክሂድ ማርቲን ኮርፖሬሽን የመጀመሪያውን ምርት በፈረንጆቹ 2024 እንደሚያስረክብ ይጠበቃል።

አሜሪካ ለዩክሬን ተመሳሳይ የሮኬት ማስወንጨፊያዎችን የሰጠች ሲሆን፣ የኢስቶኒያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳለው፣ መሳሪያዎቹ የሩሲያን መሳሪያ ማከማችዎችን፣ የመጓጓዣ መስመሮችን፣ የዕዝ ማዕከላትን ኢላማን ሳይስቱ ባተሳካ ሁኔታ አውድመዋል።

ዘገባው የአሶሴይትድ ፕረስ ነው።

XS
SM
MD
LG