በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን የሚገኙ ራስታዎች ጭቆናው በርትቶብናል ይላሉ


በሱዳን የራስ ተፈሪ ልምድ ተከታዮች አንዱ (ፎቶ ፋይል)
በሱዳን የራስ ተፈሪ ልምድ ተከታዮች አንዱ (ፎቶ ፋይል)

በሱዳን የሚገኙ ራስታዎች ከፍተኛ ጭቆና ቢደርስባቸውም፣ መብታቸውን ለማስከበር እንደሚታገሉ በመናገር ላይ ናቸው።

ለረጅም ዘመናት ጭቆና እንደሚደርስባቸው የሚናገሩት የሱዳን ራስታዎች፣ ጫናው እንደ አዲስ እየበረታብን ነው ይላሉ።

የ31 ዓመቱ አህመድ የራስ ተፈሪ ወግና ልማድ ተከታይ ሲሆን፣ ራስታ “እውነትን የሚናገር፣ ደፋርና ለሌሎች ሰዎች መብት የሚታገል” ማለት ነው ሲል ይገልጸዋል።

በሱዳን የሚገኙ የራስታ ተከታዮች ቁጥር በግልጽ የማይታወቅ ሲሆን፣ በ30 ዓመታት የኦማር አል በሽር አገዛዝ ወቅት ተደብቀው ይኖሩ እንደነበር ይነገራል።

“አል በሽር በመውደቁ ደስተኛ ነበርን” ብሏል የሬጌው ሙዚቃ አቀንቃኝ ባብ ማርሊ አፍቃሪ የሆነው አህመድ። እርሱም በአንድ የሥነ ጥበብ አውደ ርዕይ ላይ ከሙዚቃ ቡድኑ ጋር ሬጌ ይጫወታል።

ነጻነታችን ግን ብዙ አልቆየም ይላሉ የሱዳን ራስታዎች።

አል ቡርሃን ስልጣን መንጠቃቸውን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ በርካታ የራስ ተፈሪ ልምድ ተከታዮች ተገድለዋል ብሏል የኤ.ኤፍ.ፒ. ዘገባ።

XS
SM
MD
LG