በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ህብረት ሚኒስትሮች አዲስ የስደተኞች እቅድ አፀደቁ


አንድ ስደተኛ በአውሮፓ የባህር-ሰብአዊ ድርጅት ከታደገ በኋላ በቱሎን፣ ፈረንሳይ ህዳር 11 ቀን 2022 ከ'ኦሽን ቫይኪንግ' መርከብ ሲወርድ
አንድ ስደተኛ በአውሮፓ የባህር-ሰብአዊ ድርጅት ከታደገ በኋላ በቱሎን፣ ፈረንሳይ ህዳር 11 ቀን 2022 ከ'ኦሽን ቫይኪንግ' መርከብ ሲወርድ

የስደተኞች አዳኝ ጀልባን በተመለከተ በጣሊያን እና በፈረንሳይ መካከል የተነሳ ውዝግብን ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት የስደተኞችን አቀባበል በተሻለ ሁኔታ ለማስተባበር ያስችላል ሲል ያወጣውን እቅድ የአውሮፓ የሀገር ውስጥ ሚኒስትሮች ተቀብለውታል።

በዚህ ወር መጀመሪያ ጣሊያን መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት የሚተዳደረውን መርከብ በመመለስ የባህር ህግን ጥሳለች ስትል ፈረንሳይ ክስል ያቀረበች ሲሆን፣ ይህም ፖለቲካዊ አወዛጋቢ በሆነው ጉዳይ ላይ የአውሮፓ ህብረት አዲስ የቀውስ ንግግር ብራስልስ ላይ እንዲያካሂድ አስገድዶታል።


ውይይቱ ውጤታማ እንደነበር ቢገለፅም ግን የአውሮፓ ህብረትን በሊቀመንበርነት የምትመራው ቼክ ሪፐብሊክ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ቪት ሬኩሳን ሁሉም ተሳታፊዎች "ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ከዚህም የበለጠ መደረግ አለበት" ማለታቸውን ገልፀዋል።

የጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር እ.አ.አ በ2015 እና 2016 ከነበረበት እጅግ ያነሰ ቢሆንም በሁለቱ ሀገራት የተፈጠረው አለመግባባት 27ቱ የህብረቱ ሀገራት ጥገኝነት ጠያቂዎችን እኩል ለመከፋፈል የደረሱበትን ስምምነት አፍርሷል።

በዚህ ወር መጀመሪያ በቀኝ ዘመም መሪው ጆርጂያ ሜሎኒ የሚመራው የጣሊያን መንግስት የኖርዌይ ባንዲራ የያዘች መርከብ በሜዲትራኒያን ባህር ከመስጠም የዳኑ 234 ስደተኞችን ይዛ እንዳትገባ ከልክሏል።

በዚህ ምክንያት "ኦሽን ቫይኪንግ" የተሰኘችው መርከብ ወደ ፈረንሳይ በማቅናቷ ቀደም ሲል በጣሊያን መሄጃ ያጡ 3ሺህ 500 ጥገኝነት ጠያቂዎችን እንድትወስድ የተደረሰውን ስምምነት ጥሳለች ሲሉ የፈረንሳይ ባለስልጣናት ለሮም አቋም ቁጣ ያዘለ ምላሽ ሰጥተዋል።


አዲሱ የአውሮፓ ህብረት እቅድ ህገወጥ ስደተኞች በህገወጥ አዘዋዋሪዎች መርከብ እንዳይሳፈሩ አስቀድሞ ለመከላከል ብራስልስ ከቱኒዢያ፣ ሊቢያ እና ግብፅ ጋር አብራ እንድትሰራ የሚያስችል ነው።

XS
SM
MD
LG