በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማሊያ ወታደራዊ ጥቃት ቢያንስ 100 የአል-ሻባብ ታጣቂዎች ተገደሉ


በአል-ሻባብ ይደረሰ ጥቃት
በአል-ሻባብ ይደረሰ ጥቃት

የሶማሊያ ጦር እና አጋር የጎሳ ሚሊሺያዎች በማዕከላዊ ሸበሌ ክልል ባካሄዱት ወታደራዊ ጥቃት ቢያንስ 100 የአል-ሻባብ ታዋጊዎች መግደላቸውን የሀገሪቱ የመረጃ ሚኒስቴር ዛሬ አስታወቁ። ከቀናት በፊት በደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል፣ በታችኛው ሸበሌ ሌሎች 49 የአልሻባብ ታጣቂዎች መገደላቸውን አስታውቀው ነበር።

የመረጃ ምክትል ሚኒስቴር የሆኑት አብድራህማን ዩሱፍ አብደላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ወታደራዊ ጥቃቱ የተካሄደው ታጣቂው ሀይል በክልሉ የመንግስት ኃይሎች ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እያካሄዱት የነበረውን ለመጨረሻውን ዝግጅት ለማደናቀፍ ነው ብለዋል። አክለውም "ታጣቂዎቹ ሰራዊታችን ላይ ሙሉ ጥቃት ለማድረስ እየተዘጋጁ መሆኑን በድረሰን የደህንነት መረጃ መሰረት እቅዳቸውን ለማደናቀፍ እና ለመከላከል የተወሰደ ርምጃ ነው" ብለዋል።

የብሄራዊ ጦር ሰራዊቱ የቴሌግራም መገኛ እንደሆነ በተገለፀ ድህረገፅ በዓየር ላይ የተነሱ እና የሞቱ ሰዎች ሬሳ ክምችት የሚያሳይ ፎቶዎች ታይተዋል። የአሜሪካ ድምፅ ግን ፎቶዎቹን በገለልተኛ መንገድ ማጣራት አልቻለም።


የሶማሌ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ ከነሀሴ ወር ጀምሮ በዩናይትድ ስቴትስ እና የጎሳ ሚሊሺያዎች ድጋፍ የተቀናጀ ጥቃት መክፈታቸውታቸውን ተከትሎ አል-ሻባብ ከፍተኛ ጫና እየደረሰበት መሆኑ ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG