በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታንዛኒያ በድርቁ ምክንያት መብራት በፈረቃ ማከፋፈል ጀመረች


ታንዛኒያ በድርቁ ምክንያት መብራት በፈረቃ ማከፋፈል ጀመረች
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:35 0:00

ታንዛኒያ በድርቁ ምክንያት መብራት በፈረቃ ማከፋፈል ጀመረች

ታንዛኒያ በድርቁ ምክንያት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት አቅሟ በመቀነሱ መብራት በፈረቃ ማከፋፈል እንደምትጀምር አስታወቀች፡፡

የሀገሪቱ የኤሌክትሪክ ኅይል አቅርቦት ኩባኒያ (ታኔስኮ) በየዕለቱ አስከ ግማሽ ቀን የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች እንደሚኖሩ አስታውቋል፡፡

የንግድ መዲናዋ ዳሬሰላም ውሃ በፈረቃ ማከፋፈል ከጀመረች ሰንብታለች፡፡

የዳሬሰላም ነዋሪው ራማዳን ኢብራሂም የተነፈሱ የመኪና እና የሞተር ቢስኪሌት ጎማዎችን አየር በመሙላት ወይም በጎሚስታ ስራ ነው የሚተዳደረው፡፡

አሁን ግን ባለው የኤሌክትሪክ አቅርቦት ችግር የተነሳ ስራው መቋረጡን ገልጿል፡፡ “በጎሚስታ ስራችን ለዕለት ኑሮ ወጪያችን የሚሆን ትንሽ ገቢ እናገኝበት ነበር፡፡

መሳሪያው የሚሰራው በኢሌክትሪክ ነው፡፡ አሁን ኤሌክትሪክ የለም፤ መቼ እንደሚመጣም አናውቅም፡፡ ስለዚህ በተቋረጠ ቁጥር ስራ ማቆም አለብን” ብሏል ኢብራሂም፡፡

የታንዜኒያ ባለሥልጣናት በተራዘመው ድርቅ እና አንዳንዶቹ ማመንጫዎች ዕድሳት ላይ በመሆናቸው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መቀነሱን ተናግረዋል፡፡ በቀን እስከዘጠኝ ዘጠኝ ሰዓት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች አሉ፡፡

የሀገሪቱ የኤሌክትሪክ ኃይል ኩባኒያው (ታኔስኮ) ዋና ሥራ አስኪያጅ ማሃራጌ ቻንዴ እንዳሉት በየቀኑ ከሦስት መቶ አስከ ሦስት መቶ ሃምሳ ሜጋ ዋት ዕጥረት ያጋጥማል፡፡

አሁን ለአጭሩ ጊዜ ትኩረታችንን በነዳጅ ተቋማታችን ላይ እንዲሁም የኤክትሪክ ሃይል ማመንጫዎች ዕድሳት ላይ አድርገን እየሰራን ነን ብለዋል፡፡

ታንዛኒያ በጀመረችው የጁሊየስ ኔሬሬ ግድብ ግንባታ መርኃግብሯ አማካይነት የኤሌክትሪክ ኅይል አቅሟን ለማሳደግ በመስራት ላይ ስትሆን ሥራው ሲጠናቀቅ 2115 ሜጋዋት ያመነጫል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

አንደቬናንስ ማጁላ ያሉ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ተሟጋቾች በበኩላቸው የአየር ንብረት ለውጥ ሀገሪቱ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመታገል የበለጠ መሰራት እንዳለበት ያሳስባሉ፡፡

የተፈጥሮ አካባቢ እንክብካቤን አካባቢን በማይጎዳ መንገድ ማረስ እና በታዳሽ የኅይል ምንጭ ላይ የበለጠ መዋዕለ ነዋይ መመደብ አስፈላጊ መሆኑን ያነሳሉ፡፡ ለዚህ ተገቢ የሆነውን መርኃ ግብር ቀርጾ መስራት ካልተጀመረ የአየር ንብረት ለውጥ በውሃ እና በኅይል

ምንጭ አቅማችን ላይ ፈተና መደቀኑ የማይቀር ነው፡፡ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ያጋጠሙንን ጎርፍ እና ድርቅ የመሳሰሉ ከባድ አደጋዎችም ይቀጥላሉ”ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG