በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ 3ቱን የአልሸባብ መሪዎች ለጠቆመ የምትሰጠውን ሽልማት ወደ 10 ሚሊዮን ዶላር አሳደገች 


የአል ሻባብ ተዋጊዎች
የአል ሻባብ ተዋጊዎች

የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ሶስቱን የሶማልያ ሽብርተኛ አልሸባብ ቡድን መሪዎች ለመያዝየሚያግዝ መረጃ ለሚሰጡ ሰዎች የሚሰጠውን የገንዘብ ወሮታ እስከ 10 ሚሊዮን ማሳደጉን አስታወቀ፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ዜግነት ያለውን ግለሰብና ለላፉት 14 ዓመታት የቡድኑ ከፍተኛ መሪዎች የሆኑትን ሁለቱን ግለሰቦች ጨምሮ አህመድ ድሪዬ፣ ማሃድ ካራቴና ጂሃድ ሙስጠፋ የተባሉትን ሶስቱን ሰዎች ፍለጋ የሶማልያ ዜጎችና በአካባቢው የሚገኙ አገሮች እንዲተባበሩም የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ጠይቋል፡፡

ሶስቱ ግለሰቦች ሶማልያ እና ኬንያ ውስጥ ብዙ ሰዎች ለሞቱባቸው ጥቃቶች በተጠያቂነት የተከሰሱ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

በሶማልያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ላሪ አንድሬ ዛሬ ናይሮቢ ኬንያ ውስጥ በሰጡት መግለጫ አዲሱ የ10 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ሽልማት ከዚህ በፊት ከነበረው ወሮታ በእጥፍ መጨመሩን ተናግረዋል፡፡

የሶማልያ መንግሥት ከአልቃይዳጋር ግንኙነት ያለውን አልሻባብን ድል በመንሳት እያደረገ ያለውን ጥረት ማድነቃቸውንም የቪኦኤ ሶማልኛ ክፍል ዘጋቢያችን ሞሃመድ ዩሱፍ ከናይሮቢያ ኬንያ የላከው ዘገባ አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG