በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ በከኼርሰን የሚገኙ የዩክሬን ወታደሮችን ጎበኙ


ፕሬዘዳት ዘለንስኪ በከኼርሰን የሚገኙ የዩክሬን ወታደሮችን ጎበኙ
ፕሬዘዳት ዘለንስኪ በከኼርሰን የሚገኙ የዩክሬን ወታደሮችን ጎበኙ

ዛሬ ሰኞ ነጻ በወጣችው የከኼርሰን ከተማ ተገኝተው የዩክሬን ወታደሮችን የጎበኙት ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ “ዩክሬን ለሰላም ዝግጁ ናት ሰላም ለመላው የአገራችን ሲሉ” ተናገሩ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ከኼርሰን የተገኙት የሩሲያው ወታደሮች ከደቡባዊ ከተማ ካፈገፈጉ ቀናት በኋላ መሆኑን ተመልክቷል፡፡

ዜለንስኪ ትናንት እሁድ ባሰሙት እለታዊ ንግግራቸው በከኼርሰን ያለው ሁኔታ አሁንም በጣም አደገኛ መሆኑን እንዳይዘነጉ ዩክሬናዊያኑን አሳስበዋል፡፡

“ከሁሉም በላይ የተቀበሩ ፈንጂዎች አሉ ሁሉም የከኼርሰን ነዋሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስባለሁ” ብለዋል ዜለንስኪ፡፡

ፕሬዚዳንቱ አክለውም የሩሲያ ጦር መግባት በቻለባቸው ሌሎቹ የአገራችን ክፍሎች እንዳደረገው ሁሉ ከኼርሰንም ውስጥ ተመሳሳይ የሆኑ በርካታ ግፎችን ትቶ ሄዷል። እያንዳንዱን ገዳይ የምናገኝ ሲሆን ወደ ፍትህ እናመጣዋለን፡፡ ያለምንም ጥርጥር” ብለዋል፡፡

የዩክሬን ባለሥልጣናት ትናንት እሁድ ምግብ ውሃና መድሃኒቶችን በመያዝ፣ የሩሲያ ወታደሮችጦርነቱ ሲጀመር ጀምሮ ይዘውት ወደ ነበረው፣ አሁን ትተው ወደ ሄዱትና ስትራቴጂክ በሆነቸው የክፍለ ግዛቱ ዋና ከተማ ከኸርሰን መግባት መጀመራቸው ተነገሯል፡፡

XS
SM
MD
LG