በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እንግሊዝ እና ፈረንሳይ ወደ እንግሊዝ የሚያቋርጡ ፍልሰተኞችን በጋራ ለመግታት ተስማሙ   


ወደ እንግሊዝ የሚያቋርጡ ፍልሰተኞች
ወደ እንግሊዝ የሚያቋርጡ ፍልሰተኞች

እንግሊዝና ፈረንሳይ የእንግሊዝን የባርህ ሰርጥ አቋርጠው ወደ እንግሊዝ የሚገቡ ፍልሰተኞችን ለመግታት የጋራ ኃይል መሰረቱ፡፡

በአዲሱ ስምምነት መሰረት ትናንሽ ጀልባዎችን በመያዝ አደገኛ የሆነውን ውሃ አቋርጠው ወደ እንግሊዝ ለመግባት የሚሞክሩ ፍልሰተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎችን መከላከል የሚያስችላትን ደህንነት እንድታጠናክር፣ እንግሊዝ ለፈረንሳይ 75 ሚሊዮን ዶላር ትከፍላለች፡፡

ስምምነቱ የአሰሳውን ቁጥጥር፣ ድሮን እና ድንበር ማቋረጥን የሚከላከሉ ሌሎች ቴኮኖሎጂዎችን በ40 ከመቶ እንደሚጨምር ተመልክቷል፡፡

ሁለቱ አገሮች ህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችንና ከተያዙ ፍልሰተኞች የተገኙ ሌሎች ስጋቶችን በተመለከተ መረጃዎችን እንዲለዋወጡ ስምምነቱ የሚያዝ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ስምምነቱን ፓሪስ ላይ ዛሬ ሰኞ የፈረሙት የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ጄራልድዳርማኒን እና የእንግሊዝ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሱኤላ ብራቨርማን መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG