በኢስታንቡል፣ ቱርክ ሰዎች በብዛት በሚያዘውትሩት አውራጎዳና ላይ በደረሰ ፍንዳታ አራት ሰዎች ሲሞቱ፣ 38 ደግሞ ቆስለዋል።
የፍንዳታው ምክንያት ወዲያውኑ አልታወቀም።
አሶስዬትድ ፕረስ የቱርክ መንግስታዊ የዜና ወኪል የሆነውን አናዶሉ ጠቅሶ እንደዘገበው፣ አራት አቃቢያነ ህጎች ፍንዳታውን እንዲመረምሩ ተመድበዋል።
በመረጃ መረብ የተለቀቀና የፍንዳታው መሆኑ የተነገረ ቪዲዮ፣ ከከባድ ፍንዳታ ጋር እሳት ሲቀጣጠልና ሰዎች ራሳቸው ለማዳን ሲራኮቱ አሳይቷል።
የቱርክ የመገናኛ ብዙሃን ጠባቂ የሆነው ተቋም፣ ፍንዳታውን በተመለከተ ግዜያዊ እግዳ በመጣሉ፣ ማሠራጫ ጣቢያዎች የፍንዳታውንም ሆነ ከፍንዳታው በኋላ ያሉ ሁኔታዎችን በቴሌቭዥን እንዳይሳዩ ተከልክለዋል።
የኢስታምቡሉ አግረ ገዢ አሊ የርሊካይ የሟቾቹንና የተጎጂዎቹን ቁጥር በተመለከተ በትዊተራቸው አስታውቀዋል።