በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩክሬን የመቃብር ስፍራዎች መጨመራቸውን የሳተላይት ምስሎች አመላከቱ


የዩክሬን መድፍ ተኳሽ ወታደር
የዩክሬን መድፍ ተኳሽ ወታደር

አሶሽየትድ ፕሬስ በመረመራቸው የሳተላይት ፎቶዎች የሩሲያ ሃይሎች የወደብ ከተማ የሆነችውን ማሪፖልን ከተቆጣጠሩ ከወራት በኋላ በደቡባዊ ዩክሬን የመቃብር ስፍራ በፍጥነት እየተስፋፋ መሆኑን ማመላከታቸውን ዛሬ አስታውቋል።

የፕላኔት ላብስ ፒቢሲ ምስሎች በሰሜን ምዕራብ የሃገሪቱ ክፍሎች በቁጥጥር ስር ባለችው ስታሪ ክሪም በተሰኘች ቦታ ያለውን የመቃብር ስፍራ አጉልተው ያሳያሉ። በከተማዋ ደቡባዊ ክፍል ያለው የመቃብር ስፍራ እ.ኤ.አ በመጋቢት 24 ማሪፖል በሩሲያ ጥቃት ስር ሳለች የነበረውን በጥቅምት 14/2022 ካለው ጋር ያመሳከረ ሲሆን፤ የመቃብር ስፍራው በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ያመላክታል።

በመቃብር ስፍራው ደቡብ ምዕራብ ክፍልም 1.1 ኪ.ሜ የሚሆነው ስፍራ በቅቡ የተቆፈረ ትኩስ መቃብር መሆኑ ከምስሉ ላይ ይታያል። በተመሳሳይ በመቃብሩ ስፍራ ደቡብ ምዕራብ አንጻር ደግሞ ከግማሽ ስኩዌር ኪ.ሜ የሚሆን መሬት ተቆፍሯል።

እስካሁን ድረስም ባለፉት ሰባት ወራት ይሄ ሁሉ ሰው ከየት መጥቶ ሊቀበር እንደቻል ግልጽ የሆነ ነገር የለም።

መቀመጫውን በለንደን ያደረገው የመረጃ ኢንፎርሜሽን ሪዚሊየንስ (መረጃ መቋቋም) የተሰኘ ግብረሰናይ ተቋም ስታሪ ክሪም በተሰኘው የመቃብር ስፍራ ላይ ባደረገው ክትትል፤ ሩሲያ ዩክሬን ላይ ጦርነት ከከፈተችበት ጊዜ አንስቶ 4600 የሚሆኑ መቃብሮች መቆፈራቸውን አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG