በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩክሬን ጦርነትን ማስቆም የሚችለው ዲፕሎማሲ ብቻ ነው ሲሉ ዓለም አቀፍ መሪዎች ጥሪ አቀረቡ


'አረጋውያን' የተሰኘው ቡድን አባላት ዛይድ ራአድ አል-ሁሴን፣ ሜሪ ሮቢንሰን እና ኤርኔስቶ ዘዲሎ የቀድሞው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ ባን ኪሙን ለአሶሽዬትድ ፕሬስ የሚያደርጉትን ገለፃ ሲያዳምጡ
'አረጋውያን' የተሰኘው ቡድን አባላት ዛይድ ራአድ አል-ሁሴን፣ ሜሪ ሮቢንሰን እና ኤርኔስቶ ዘዲሎ የቀድሞው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ ባን ኪሙን ለአሶሽዬትድ ፕሬስ የሚያደርጉትን ገለፃ ሲያዳምጡ

በዩክሬን እየተካሄደ ያለው አውዳሚ ጦርነት ሊቆም የሚችለው በውይይት እና ዲፕሎማሲ ብቻ ሲሆን የጦር ሜዳ ድል ለሁለቱም ተዋጊ ወገኖች የማይቻል ነው ሲሉ በኔልሰን ማንዴላ የተመሰረቱት የቀድሞ የዓለም መሪዎች ቡድን አባላት ተናገሩ።

'አረጋውያን' በሚል ስያሜ የሚታወቀው ቡድን መልዕክቱን ለዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ሲያስተላልፍ ከግጭቱ መውጫ መንገዶችን ማጤን እንዳለባቸው እንደነገሯቸው የቡድኑ ሊቀመንበር የሆኑት የቀድሞ የአየርላንድ ፕሬዝዳንት ሜሪ ሮቢንሰን ከአሶሼትድ ፕሬስ የስራ ሃላፊዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ተናግረዋል።


የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሆነው ያገለገሉት ሮቢንሰን ሲያስረዱ "በሁለቱም ወገኖች በኩል ወታደራዊ ትጥቅ ከመጨመር እና በዩክሬን ህዝብ ላይ የሚደርሰውን ውድመት ከማባባስ በተቃራኒ፣ ይሄ ሁኔታ መብቃት አለበት የሚለውን ሀሳብ ለማራመድ፣ እንዴት ማቆም ይቻላል የሚለውን አስተሳሰብ የበለጠ ማበረታታት አለብን" ብለዋል።

ቀደም ሲል የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር የነበሩት ዛይድ ራአድ አል-ሁሴን በበኩላቸው ጦርነቱ ሊቆም የሚችለው በዲፕሎማሲ እና በድርድር ብቻ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው፣ ይህ ማለት ግን ዩክሬን ያለምንም ምክንያት የራሺያ ጥቃት ሰለባ እንደመሆኗ ሉዓላዊነቷን አሳልፋ እንድትሰጥ መጠየቅ ማለት እንዳልሆነ ተናግረዋል።


አክለውም የግጭቱ እልባት ሊሆን የሚችለው ሩሲያ 'ከሌላ አቅጣጫ' ሲሉ ከገለፁት እና ምናልባት ከሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን (ኔቶ) ወይም ከአባል ሀገራቱ ከአንዱ ሊሆን ከሚችል ሀገር፣ መተማመኛ ስታገኝ ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋል። የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የምዕራቡ ዓለም ወደ ድምበራቸው እየተጠጋ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ሲያሰሙ የቆዩ ሲሆን ላካሄዱት ወረራም እንደምክንያትነት ይጠቅሱታል።

XS
SM
MD
LG