በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሠላም ሥምምነቱን ተከትሎ የመብት ድርጅቶች ሀሳባቸውን እየገለጡ ነው


የሠላም ሥምምነቱን ተከትሎ የመብት ድርጅቶች ሀሳባቸውን እየገለጡ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:58 0:00

የሠላም ሥምምነቱን ተከትሎ የመብት ድርጅቶች ሀሳባቸውን እየገለጡ ነው

ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን ሂዩማን ራይትስ ዋች በኢትዮጵያ መንግሥትና በህወሓት ባለሥልጣናት መካከል በዚህ ሳምንት መጀመሪያ የተደረሰበት የተኩስ አቁም ሥምምነት “ተጨማሪ የጭካኔ ድርጊቶችና ሰብአዊ አደጋዎችን ለመከላከል አፋጣኝ እና ጥብቅ የሆነ ዓለም አቀፍ ክትትል እንዲኖር ወሳኝ እድል ይፈጥራል” ሲል ዛሬ አርብ ባወጣው መግለጫ ገለጸ።

ድርጅቱ “የግጭቱ ተሳታፊ በሆኑ ሁሉም ወገኖች፣ ህገ ወጥ ግድያን፣ አስገድዶ መድፈርና ጾታዊ ጥቃት፣ ህገ ወጥ የከባድ መሳሪያ ደብደባ፣ የአየር ጥቃትና በጦርነት ወቅት የሚጸምን ዘረፋ ጨምሮ ከፍተኛ የሆኑ በጦርነት ወቅት መከበር ያለባቸው ህጎችና የሰብአዊ መብቶች” መፈጸማቸውን መመዝገቡን ተናግሯል፡፡

በሥምምነቱም የትግራይ አማጺ ቡድን ትጥቁን እንዲፈታ በልዋጩም ከሃገሪቱ ጦር ሰራዊት ጋር መልሶ ማዋሃድ እና ብሄራዊው ጦር ወደ ክልሉ እንዲመለስ የሚሉት ይገኙበታል። ይሁንና እንደ ባለሙያዎች ዕይታ በሁለቱ ወገኖች መካከል ባለው አለመተማመን ይህን የስምምነቱን ክፍል ተግባራዊ ማድረግ አዳጋች ሊያደርገው ይችላል” ይላሉ ፡፡

በአፍሪካ ቀንድ የዓለም አቀፍ ስትራቴጂያዊ ጥናት ተቋም የግጭቶች አፈታት ባለሙያ ሙስጠፋ ዩሱፍ አሊ የሥምምነቱ አፈጻጸም “በተቀናጀ እና ቅደም ተከተሉን የጠበቀ” መሆን ይገባዋል ይላሉ፡፡ ባለሙያው አያይዘውም “ትጥቅ የማስፈታቱ ሥራ በሥምምነቱ በተገለጸው መሰረት በሚተገበርበት ወቅት” በሁለቱም ወገኖች መካከል ትምምን መጎልበት አለበትግደ” ይላሉ፡፡

“ቁስሉ ማጥገግ አለበት።” ያሉት ባለሙያው “ኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጸሙት ለእነኚህ አንዳንድ ዘግናኝ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች አንድ የእውነት አፈታት የፍትህና የእርቅ ኮሚሽን ያስፈልጋል፡፡ ምናልባትም በሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች የሚከናወን፡፡” ብለዋል፡፡

በትግራይ ኃይሎችና በፌደራል መንግስቱ ወታደሮች እንዲሁም የኢትዮጵያ አጋር የሆነችውን ኤርትራን ጨምሮ በትግራይ እና በአጎራባች ክልሎች የተካሄደው ጦርነት ከተጀመረ ዛሬ ጥቅምት 25 አራተኛ ዓመቱን ደፍኗል፡፡

በኢትዮጵያ መንግሥትና ህወሓት መካከል ግጭቱን የማቆም ስምምነት የተደረሰው በአፍሪካ ኅብረት ሸምጋይነት እና በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ መሪነት፣ ደቡብ አፍሪካ ዋና ከተማ ፕሪቶሪያ ውስጥ ለ10 ቀናት ከተደረገው ድርድር በኋላ ከትናንት በስቲያ ረቡዕ መሆኑ ይታወሳል፡፡

XS
SM
MD
LG