በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመንግስታቱ ድርጅት በምዕራብ እና ማዕከላዊ አፍሪካ በጎርፍ ሳቢያ 3.4 ሚሊየን ሰዎች መፈናቀላቸውን አስታወቀ


በጎርፍ መጥለቅለቅ በናይጄሪያ
በጎርፍ መጥለቅለቅ በናይጄሪያ

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት በምዕራብ እና በማዕከላዊ አፍሪካ በጎርፍ አደጋ በደረሰ ጥፋት ምክንያት 3.4 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች ከመኖርያ ቀያቸው መፈናቀላቸውን ትላንት ዐርብ ባወጣው መግለጫ ይፋ አደረገ።

የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ከ218 ሚሊየን በላይ ህዝብ ባላት በናይጄርያ ባለፉት አስር ዓመት ውስጥ በደረሰ የጎርፍ አደጋ 3.4 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ሲሞቱ፣ 1.3 ሚሊየን የሚሆኑ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን እና ከ2.8 ሚሊዮን ሰዎች በላይ መጎዳታቸውን አመልክቷል።

በጎርፍ ውሃ ምክንያት የተለያዩ መሰረተ ልማቶች እና እርሻ ስፍራዎች በመናጋታቸው ነዋሪዎች ወደ ከፍተኛ ቦታዎች ለመሸስ እንደተገደዱ ተቋሙ ጨምሮ አስታውቋል። አብዛኞቹም ግጭት እና ረብሻ

ካሉባቸው የሃገሪቱ ክፍሎች የተፈናቀሉ ሰዎች ባሉባቸው የመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ እየኖሩ ይገኛሉ።

“የአየር ንብረት ቀውስ የሰዎችን ገቢ በማቃወስ፣ የምግብ ዋስትናን በማወክ እና ከሃብት እጥረት የተነሳ ግጭት እንዲከሰት በማድረግ ሰዎች ለመፈናቀል እየተዳረጉ ነው።” ያሉት የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ኦልጋ ሳራዶ አያይዘውም “በአየር ንብረት መቃወስ እና በመፈናቀል መሃከል ያለው ትስስር በግልጽ ሆነ እየታየና እያደገ መጥቷል” ብለዋል።

XS
SM
MD
LG