በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ለአደገኛ የፖለቲካ አጀንዳ ሲባል እየተፈጠሩ ያሉ ያለቻቸውን ውንጀላዎች አወገዘች


ኢትዮጵያ ለአደገኛ የፖለቲካ አጀንዳ ሲባል እየተፈጠሩ ያሉ ያለቻቸውን ውንጀላዎች አወገዘች
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:00 0:00

“በኢትዮጵያ ላይ ያልተረጋገጡና ፖለቲካዊ ዓላማ ያላቸውን ውንጀላዎች ከሚያቀርቡ ካላቸው ሃገሮችና ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት እንደሚያጤን” የኢትዮጵያ መንግሥት ዛሬው በሰጠው መግለጫ አመልክቷል። ይሁን እንጂ እነዚህን ሀገሮችና ተቋማት መንግሥት በስም አልጠቀሳቸውም፡፡ መግለጫውን ካወጣው ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረትም ለጊዜው አልተሳካም፡፡

በደቡብ አፍሪካ እየተካሔደ ያለው የሠላም ንግግር ዛሬ አራተኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን፣ ዩናይትድ ስቴትስ የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት እንዲቆም የጀመረችውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ገፍታበታለች፡፡ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን በዚሁ የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ዙሪያ ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ጋር ካናዳ ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት በዛሬው መግለጫው ማንነታቸውን በግልጽ ሳይጠቅስ “አንዳንዶች” ሲል የጠራቸው አካላት “የሚችሉትን ሁሉ በማድረግ ህወሓትን ለማዳን እየተረባረቡ ነው” ሲል ከሷል።

በሌላ ዜና፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ፣ “በትግራይ ክልል አድዋ ተሰማርተው በግጭት የተጎዱ ወገኖችን በማገዝ ላይ የነበሩ” ያላቸው አንድ የማኅበሩ አባል ከአድዋ ወደ ወልቃይት አዲ ረመፅ ሆስፒታል ቁስለኞችን ለማድረስ በተንቀሳቀሱበት ወቅት ቁስለኞቹን ጨምሮ በታጣቂ ሃይሎች በተደረገባቸው ጥቃት ተገድለዋል” ብሏል፡፡

XS
SM
MD
LG