ምሥራቅ ወለጋ፣ ምሥራቅና ምዕራብ ሸዋ በአየር ሲቪሎች ተገድለዋል - ኦፌኮና ኦነግ
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ፣ ምሥራቅ ሸዋና ምዕራብ ሸዋ ውስጥ ‘ሰሞኑን ተፈፅመዋል’ በተባሉ ጥቃቶች “ከመቶ በላይ ሲቪሎች ተገድለዋል” ሲል የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አቤቱታ አሰምቷል። የአየር ድብደባ እንዳልተፈፀመ ለቪኦኤ የተናገሩ ባለሥልጣናት ደግሞ “የመንግሥቱ ኃይሎች ዒላማ ሸኔ የሚሏቸው ታጣቂዎች እንጂ ሲቪሎች አይደሉም” ብለዋል። የመንግስት ኮምዩኒኬሽንስ ጽ/ቤትና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ስለተባለው ጥቃት መረጃ እንደሌላቸው ገልፀዋል።
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ሴፕቴምበር 21, 2023
የአወዛጋቢዋ አውራ ጎዳና ወይም ቆርኬ ጥቃት አጠያያቂ እንደኾነ ነው
-
ኦገስት 26, 2023
በጋሞ ዞን በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት ጠፋ
-
ኦገስት 23, 2023
በፕሪቶርያው ስምምነት ከእስር መፈታት ሲገባቸው ያልተፈቱ እስረኞች እንዳሉ ተገለጸ