በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያና ጃፓን፣ ሰሜን ኮሪያን በጋራ ለመመከት ተስማሙ 


የጃፓንና አሜሪካ የጋር የአየር ሃይል ልምምድ (ፎቶ ፋይል)
የጃፓንና አሜሪካ የጋር የአየር ሃይል ልምምድ (ፎቶ ፋይል)

የሶስቱ ሃገራት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ባላንጣቸው ላይ ለመተባበር የተስማሙት ዛሬ ቶኪዮ ላይ ባደርጉት ምክክር ነው።

“ሰሜን ኮሪያ ሰባተኛውን የኑክሌር ሙከራ የምታደርግ ከሆነ፣ ጠንከር ያለ ምላሽ አስፈላጊ መሆኑን ተስማምተናል” ብለዋል የደቡብ ኮሪያው ምክትል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቾ ያን-ዶንግ።

ሰሜን ኮሪያ በዚህ ዓመት በርካታ የኑክሌር ሙከራዎችን አድርጋለች። በዚህ ወር በጃፓን የአየር ላይ ያስወነጨፈችው ባሊስቲክ ሚሳዬል ተጠቃሽ ነው።

የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝደንት ዩን ሶክ ዮል ትናንት ማክሰኞ እንደተናገሩት ፒዮንግያንግ የኑክሌር ሙከራ ለማድረግ ዝግጅቷን አጠናቃለች። ይህም ከእ.አ.አ 2006 ወዲህ ሰባተኛው መሆኑ ነው።


ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በፊት ጃፓን ደቡብ ኮሪያን ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ጠቅልላ መያዟን ተከትሉ በሁለቱ ሃገራት መካከል ፍቅር ባይኖርም፣ የሰሜን የጋራ ባላጣቸው የጦር መሣሪያ ሙከራ መቀጠል ሁለቱን ወገኖች ያቀራረበ ይመስላል።

“የኑክሌር ሙከራን ጨምሮ ተጨማሪ ትንኮሳ ባለበት ሁኔታ፣ ቀጠናዊ የመከላከል ብቃታችንን ለማጠናከርና በዲፕሎማሲ ረገድ አብረን ለመሥራት ተስማምተናል” ሲሉ የጃፓኑ ምክትል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ተናግረዋል።

የአሜሪካው ምክትል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ወንዲ ሸርማን፣ ሰሜን ኮሪያ ተጨማሪ ትንኮሳ ከማድረግ እንድትቆጠብና ዩናይትድ ስቴትስ አሁንም ካለቅድመ ሁኔታ ለመነጋገር እንደምትፈልግ አስታውቀዋል።

የአሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያና ጃፓን የጦር መርከቦች ባለፈው ወር የባሊስቲክ ሚሳዬል መከላከል በተመለከተ ልምምድ አድርገዋል።

XS
SM
MD
LG