በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩክሬን ጥቅም ላይ ውለዋል የተባሉ የኢራን ድሮኖችን በተመለከተ እስራኤል ለአሜሪካ መረጃ ልትሰጥ ነው 


ጆ ባይደንና አይሳክ ሄርዞግ (ፎሮ ፋይል)
ጆ ባይደንና አይሳክ ሄርዞግ (ፎሮ ፋይል)

የእስራኤሉ ፕሬዝደንት አይሳክ ሄርዞግ በሩሲያ ጥቅም ላይ የዋሉትን የኢራን ድሮኖች በተመለከተ ሃገራቸው ያላትን መረጃ ዛሬ የአሜሪካውፕሬዝደንት ጆ ባይደንን ሲያገኙ እንደሚያካፍሏቸው አቅደዋል ተብሏል።

የሄርዞግ ቢሮ እንዳለው በዩክሬን ጥቅም ላይ የዋሉትንና ባለፈው ዓመት በኢራን የተሞከሩትን ድሮኖች ተመሳሳይነት የሚያሳዩ ፎቶዎች እስራኤል አላት።

ዩክሬንና የምዕራብ አጋሮቿ ሩሲያ የዩክሬን መዲና ኪቭን ጨምሮ ለመደብደብ የተጠቀመችባቸው ድሮኖች ኢራን ሠር የሆኑ ሻሂድ-213 የተባሉ ድሮኖች መሆናቸውን ሲናገሩ ሰንብተዋል።

ኢራን ለሩሲያ ድሮኖቹን ማቀበሏን ትክዳለች፤ ሩሲያም ድሮኖቹን በዩክሬን ላይ መጠቀሟን እንዲሁ።

ትናንት ማክሰኞ ጆ ባይደን ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ለሩሲያ ልከዋል፤ በተለይም ደርቲ ቦምብ በሚባል የሚታወቀውን መሳሪያ ወይም ሌላ የኑክሌር መሣሪያ ሩስያ በዩክሬን ላይ የምትጠቀም ከሆነ።

XS
SM
MD
LG