በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪቃ ሕብረት መሩ የሰላም ንግግር ተጀመረ


አፍሪቃ ሕብረት መሩ የሰላም ንግግር ተጀመረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:47 0:00

አፍሪቃ ሕብረት መሩ የሰላም ንግግር ተጀመረ

የኢትዮጵያ መንግስት እና የሕወሃት የሰላም ንግግር ዛሬ መጀመሩን የአፍሪካ ሕብረት አስታወቀ።

በአፍሪካ ሕብረት መሪነት እየተካሔደ ባለው የሰላም ውይይት ላይ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ)፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የዩናይትድ ስቴትስ ተወካዮች በታዛቢነት በመሳተፍ ላይ መሆናቸውንም ሕብረቱ ዛሬ አመሻሽ ላይ ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል።

ዩናይትድ ስቴትስ በሰላም ንግግሩ ላይ በመሳተፍ ላይ መሆኗን የገለጹት የሀገሪቱ ውጭ ገዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ፣ ስምምነት ላይ እንዲደረስ የሚደረገውን ጥረት መደገፏን እንደምትቀጥልም ገልጸዋል፡፡

በተያያዘ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ግንኙነቶች ኮሚቴ ሰብሳቢ ሴናተር ባብ ሜኔንዴዝን ጨምሮ 9 የምክር ቤት አባላት፣ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በጻፉት በደብዳቤ፣ የኢትዮጵያ መንግስት በደቡብ አፍሪካው የሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ ያሳለፈውን ውሳኔ በደስታ ተቀብለው ከድርድሩ በፊት እንዲሁም ድርድሩ እየተካሔደ በሚቆይበት ጊዜ ግጭቱ እንዲቆም እና ያልተገደበ ሰብአዊ አገልግሎት እንዲካሔድ አሳስበዋል።

ለዚህ ደብዳቤ የኢትዮጵያ መንግስት በይፋ የሰጠው ምላሽ የለም፡፡

XS
SM
MD
LG